በኮንሶ ዞን በተፈጠረው ግጭቶች ከ84 ሺሕ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን ኢዜማ አስታወቀ

0
763

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ በኮንሶ ዞን በተፈጠረው ግጭት ዙሪያ ያጠናውን ጥናት ዛሬ በአዲስ አበባ ይፋ አድርጓል።
ፓርቲው በዚህ ጊዜ እንዳለው በዞኑ በተፈጠሩ ግጭቶች ከ10 ሺሕ በላይ መኖሪያ ቤቶች 198 ሺሕ 418 ኩንታል እህል ከ100 ሺሕ በላይ የግብርና መሳሪያዎች እና ቁሳቁሶች እንዲሁም ከ32 ሺሕ በላይ የቤት እንስሳት ወድመዋል። በግጭቱ ምክንያትም በአጠቃላይ 84 ሺህ 244 ዜጎች መፈናቀላቸውንም ፓርቲው አስታውቋል::
ከተፈናቀሉት ውስጥ 51 ሺሕ የሚሆኑት ቤት ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ እንደወደመባው ባደረግኩት ምልከታ አረጋግጫለው ብሏል ኢዜማ በመግለጫው።
በኮንሶ ዞን አሁንም ዜጎች የሰብአዊና የደህንነት ችግሮች እንደቀጠሉ ፓርቲው አስታውቋል። የምግብ ችግር ተፈናቃች ከእንስሳት ጋር በመጠለያው አብሮ መኖር የሚሞቱ ሰዎች መብዛት የታጠቁ ሀይሎች የሚያካሄዱት ዝርፊያና ንብረት ማቃጠል አሁንም የተኩስ ልውውጥ አለመቆም ዜጎችን እያሳሰቡ ያሉ ጉዳዮች ናቸው ተብሏል።

ቅጽ 2 ቁጥር 119 የካቲት 6 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here