መነሻ ገጽዜናወቅታዊፈጣኑ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ እና የኑሮ ጫና

ፈጣኑ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ እና የኑሮ ጫና

ከሰሞኑ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ቢያሳይም ፣ ይፋዊ መሆነ መንገድ በትራንፖርት ታሪፍ ላይ የዋጋ ጭማሪ አልተደረገም። ሆኖም ግን በአገራችን በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ላይ ነዳጅ መጨመሩን ተከትሎ ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ አዲስ አበባ የሚደረጉ ጉዞዎች ላይ ከግማሽ አስከ እጥፍ የሚደርስ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን አዲስ ማለዳ አረጋግጣለች።

አዲስ ማለዳ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ወደ አዲስ አበባ ከሚጓዙ ተጓዦች ለማረጋገጥ ያነጋገረችው ወጣት ነጋ ዝናቤ የሥራ ቅጥር ለመከታተል ከአማራ ክልል ራያ ቆቦ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ለመጓዝ 600 ብር እንደከፈለ ለአዲስ ማለዳ ተናግሯል።
ወጣቱ ወደ አዲስ አበባ የሚመጣው የሥራ ቅጥር ማመልከቻ አስገብቶ ለመከታተል ሲል እንደሆነ እና በፊት ከነበረው በእጥፍ ዋጋ ከፍሎ ወደ አዲስ አበባ አንዲጓዝ እንዳስገደደው ተናግሯል።
ከራያ ቆቦ አዲስ አበባ በአገር የአቋራጭ አውቶብስ ዋጋ ሕጋዊ ታሪፍ 250 ብር ሲሆን በነዳጅ መጨመር ምክንያት ባለንብረቶች ዋጋ ካልጨመራችሁ አንሄድም በማለታቸው ተጓዦች መፍትሔ እስከሚሰጥና ዋጋው ወደ ነበረበት እስኪመለስ ጉዟቸውን ለመሰረዝ የተገደዱ አንዳሉም አዲስ ማለዳ ለማረጋገጥ ችላለች።

የአጭር ርቀት ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሸከርካሪዎችም ከግማሽ ያላነሰ የዋጋ ጭማሪ አድርገዋል። የአጭር ርቀት ዋጋ ጭማሪ መኖሩን ለማረጋገጥ ባደረገችው ማጣራት ከራያ ቆቦ ከተማ ደሴ መደበኛ ታሪፍ 100 ብር ሲሆን በነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ሰበብ 150 ብር ገብቷል።
አዲስ ማለዳ ባደረገቻቸው ማጣራት አሶሳ ከተማ ያሉ አንዳንድ የባጃጅ አሽከርካሪዎች ከንግድና ኢንዱስትሪ ትራንስፖርት መምሪያ የተደረገ የተመን ለዉጥ ሳይኖር የቤንዚል ዋጋ ጨምሯል በሚል ምክንያት በራሳቸዉ ጊዜ ዋጋ በመጨመር የማስከፈል ሁኔታ በመሞከር ይህ አልሆን ሲላቸዉም አድማ የማድረግ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ መታየታቸውን ለማወቅ ችላለች።

የየካቲት ወር የነዳጅ ዋጋ ክለሳ ጭማሪ መሳየቱን ተከትሎ በአንዳንድ ከተሞች፣ በገጠር ከተሞች ሳይቀር የዋጋ ጭማሪ መታየቱ የታዘበችው አዲስ ማለዳ የኢትዮጵያ ትራንስፖርት ባለስልጣን በጉዳዩ ላይ ያለውን ምላሽ ጠይቃለች።
የባለስልጣኑ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ይግዛው ዳኘው በአገር አቀፍ ደረጃ የተደረገ ምንም አይነት የታሪፍ ማሻሻያ ጭማሪ አንደሌለ ተናግረዋል።

ኃላፊው አንደሚሉት ከሆነ በነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ምክኒያት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል የሚሰሙት የሕዝብ ቅሬታ እውነት መሆኑን ጠቁመዋል። በመሆኑም ባለስልጣኑ በግልጽ የተደረገ የታሪፍ ማሻሻያ ካልተደረገ በስተቀር ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።

ባለስልጣኑ የሰማቸውን መረጃዎችና ቅሬታዎች በመያዝ ሕገ ወጥ የዋጋ ጭማሪ በተደረገባቸው አካባቢዎች ላይ ክትትልና ቁጥጥር አንዲደረግ ለክልሎች እንደሚያሳውቅ ኃላፊው አመላክተዋል።
የትራንፖረት ሚኒስቴር በበኩሉ በአገር ደረጃ የተደረገ የታሪፍ ማሻሻያ ሳይኖር የዋጋ ጭማሪ ማድረግ በሕግ የሚያስጠይቅ ድርጊት ነው ብሏል። የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ እንዳልካቸው ጸጋዬ የዋጋ ጭማሪውን ሕገ ወጥ ተግባር ነው ብለውታል።
የክልልና የዞን ከተሞች የትራንስፖርት ዋጋ ጭማሪ መሳየቱን እና አንዳንድ ክልሎችና ከተሞች የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ሥራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች የዋጋ ጭማሪውን ሲሰሙ እንዳቆሙ አዲስ ማለዳ ካገኘቻቸው መረጃዎች ተረድታለች።
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥም ይሄው የዋጋ ጭማሪ እየታየነው የሚል ጥቆማ የደረሰው የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ትራንስፖርት ባለስልጣን የታሪፍ ማሻሻያ ጥናት አድርጌ እስከማሳውቅ ድረስ ባለበት ይቆይ ብሏል።

የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ
የኢትዮጵያ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጥር 29/2013 የየካቲት ወር የነዳጅ ዋጋ ክለሳ ባደረገው መሰረት አንድ ሊትር ቤንዚን 25 ብር ከ82 ሳንቲም በመደረጉ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ማሳየቱን ተከትሎ ከአዲስ አበባ ውጪ በአንዳንድ አካባቢዎች ያለውን የትራንስፖርት ዋጋ አዲስ ማለዳ ለማጣራት ባደረገችው ጥረት የዋጋ ጭማሪው ከግማሽ እስከ እጥፍ ድረስ መሆኑን ከተጓዦች አረጋግጣለች።

የኢፌድሪ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በ2013 በጀት ዓመት የጥር ወር የነዳጅ ዋጋ ላይ መጠነኛ ክለሳ ማድረጉን ተከትሎ መንግስት ላለፉት ሁለት አመታት 24 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ዋጋ ጭማሬ ሲሸፍን መቆየቱ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል።
አዲስ ማለዳ ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘቻው መረጃዎች እንደሚያመላክቱት የአለም የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎ በጥር ወር የነዳጅ ምርት አቅርቦት ላይ መጠነኛ የዋጋ ክለሳ መደረጉን አስታዉቋል።
መንግስት ከ2011 ዓመት ሚያዝያ ወር ጀምሮ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ቢያሳይም መንግስት ጭማሪውን በመሸፈን ላለፉት ኹለት አመታት 24 ነጥብ ኹለት ቢሊዮን ብር የዋጋ ጭማሪውን ተሸክሞ መቆየቱም መረጃው አመላክቷል።

በንግድና ኢንዱስሪ ሚኒስቴር የንግድ ዕቃዎች ዋጋ ጥናት ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክተር ካሳሁን ሙላት ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ በተጠናቀቀው የታህሳስ ወርም የነዳጅ ምርቱ አንድ ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ብር የዋጋ ጭማሪ አሣይቷል ሲሉ ተናግረዋል።
መንግስት ሁሉንም የዋጋ ጭማሪውን ሸፍኖ ከሄደ በኢኮኖሚው ላይ አሉታዊ ተጸእኖ የሚያሳድር በመሆኑ መንግስት 75 በመቶውን እንዲሸፍን እና ቀሪው 25 በመቶ በህብረተሰቡ እንዲሸፈን ተደርጎ መጠነኛ የዋጋ ማስተካከያ መደረጉን ዳይሬክተሩ አብራርተዋል።
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የንግድ ዕቃዎች ዋጋ ጥናት ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክተር ካሳሁን ሙላት ጭማሪው የመጣው የአለም የነዳጅ ዋጋ መጨመሩን ተከትሎ እንደሆነ ቢያብራሩም የኢዜማ የፖሊሲ ጥናት አስተባባሪው አማንይኹን ረዳ ግን የንግድ ሚኒስቴር በአንድ ወር ውስጥ የቤንዚን ዋጋን ወደ 20 በመቶ ያህል በማሳደግ የአንድ ሊትር የመሸጫ ዋጋን 25 ብር ከ82 ሳንቲም ማድረሱ፣ የነዳጅ ዋጋ በአለም ገበያ እምብዛም ጭማሪ ባላሳየበት ሁኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ በፍጥነት እየተተኮሰ ያለው የነዳጅ ዋጋ መንግስት የIMFን ምክር በመስማት የወጪ ንግድንና የውጭ ምንዛሬ ገቢን ለማሳደግ በሚል ሰበብ የብርን የመግዛት አቅም ያለበቂ አመክንዮ ለማዳከም በማሰብ የተከሰተ ችግር እንደሆነ ያነሳሉ።

በዚህ የተሳሳተ መንገድ ከውጭ ንግድ የምናገኘው ገቢ እምብዛም እንደማይጨምርም ይታወቃል፤ የምናስገባውም ምርት ብዙም እንደማይቀንስ ግልጽ ነው። የዋጋ ንረቱ ግን ቀስ በቀስ ከነዳጅ ወደ መደሐኒት፣ መሰረታዊ ፍጆታና ቋሚ ንብረቶች ጭምር የሚሄድ መሆኑ ግልጽ ሊሆን ይገባልም ይላሉ።

ኢኮኖሚውን ቀርቶ ገበያው እንዳረገ ያርገው በማለት ዘወትር የሚወተውቱትን አክራሪ የገበያ ሥርዓት አቀንቃኞች ምክር ሰምቶ ገደል ያልገባ አገር የለም ኢትዮጵያም የተለየች አገር አይደለችም!Ethiopia is no exception! ሲሉ በጭማሪው ላይ ያላቸውን ሀሳብ አስቀምጠል።

የኢኮኖሚ ጉዳዮችን በማንሳት የሚታወቁት ሙሼ ሰሙም አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ በነዳጅ ላይ ለሁለተኛ ጊዜ የዋጋ ጭማሪ ተደርጓል። የጭማሪው መንስኤ መንግስት በነዳጅ ላይ ሲያደርግ የነበረውን ድጎማ ማቆም አለብኝ ስላለ ነው። ይህም ሆኖ መንግስት የድግስ እና የአስረሽ ምችው ወጭውን በመቆጠብ ዙርያ ምን እንዳሰበ እና እያደረገ እንደሆነ የሚታወቅ ነገር የለም። ነማለት ጭማሪውን ለምን ? ሲሉ ያናገራሉ።

የውጭ ምንዛሪ ያሳደረብን የዋጋ ንረት እና ግሽበት መጨረሻውን እያየን አይደለም። በዚህ ወር ብቻ ግሽበት ፣ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ከ19 በመቶ በላይ በማስመዝገብ ሁለተኛው የግሽበት ታሪክ ሆኗል። ካላፉት ሶስት ዓመታት ወዲህ ደግሞ ፣ ሁሉም የመንግስት አገልግሎቶች ከመታወቂያ እደሳ ጀምሮ መብራት ፣ ውኃ ፣ ኪራይ እና መዋጮን ጨምሮ ከ100 መቶ እስከ 300 በመቶ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይተዋል።

በተቃራኒው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመንግስት ሰራተኛ እና ጡረተኛ ገቢያቸው ለዓመታት ትርጉም ያለው ለውጥ አላሳየ ፣ በዚህ ላይ ነዳጅ ከምርት ግብአትነት ጀምሮ በሁሉም ዘርፍ ያለው ተጽእኖ ከፍተኛ ስለሆነ ፣ ሊያቀጣጥል የሚችለው የዋጋ ንረት እና ግሽበት ድርብ ድርብርብ እንደሚሆን የሚጠበቅ ነው ብለዋል።

ይህ ደግሞ በቋፍ ያለውን ኑሯችንን እየተፈታተነ ነው። ስጋ እና ቅንጦቱን ትተን የእለት ፍጆታችን የሆነው ዳቦ እና እንጀራ እንኳን ከ30 በመቶ በላይ ጨምሯል።
ለውጥ ያላዩት ደሞዝተኞች ፣ ጡረተኞች እና ዝቅተኛ ስራ ላይ የተሰማሩ ዜጎች ከገቢያቸው ለተደራራቢ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ከመጋለጡም በላይ፣ ከዓመት ወደ ዓመት በሚሸጋገር ተደራራቢ ግሽበት የተነሳ የመግዛት አቅማቸው እየሟሸሸ ነው ።
ዞሮ ፣ ዞሮ ደግሞ ውጤቱ ከእለት ጉርሳቸው ውጭ ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ አቅርቦቶችን እንኳን መግዛት የማይችሉበት አስጊ ሁኔታ መፈጠሩ እየታየ አንደሆነ ያነሳሉ።
በዚህ መንገድ ኢኮኖሚያችን ከቀጠለ ፣ የዜጎች አቅም ቀስ በቀስ ተመናምኖ ፣ የእለት ፍላጎታቸንን እንኳን መሸፈን የማይችሉበት ሁኔታ እንደሚፈጠር ግልጽ ነው ። ፍላጎት አለመኖር ማለት ደግሞ አጠቃላይ ሀገራዊ የእድገት እና ኢንቨስትመንት መቀጨጭ ፣ ብሎም መጥፋት ነው። ውሎ አድሮም መንግስት ፣ ነጋዴውን እና ዜጎችን እኩል ድሃ በማድረግ ፣ ሀገርን ማክስር ነው።

በጥቅሉ ፣ የአቅርቦት ፈተና ባለባቸው አገራት ፣ አቅርቦት በሚፈለገው መጠን እስካላደገ ድረስ የደሞዝ ጭማሪ ፍላጎትን ከመለጠጥ እና ዋጋን ከማናር ውጭ፣ የመግዛት አቅምን ማሻሻል አይችልም። በሌላ በኩል ደግሞ ድጎማ የአጭር ጊዜ (Short term) መፍትሔ ከመሆን ውጭ፣ መሰረታዊ ችግሮችን አይፈታም። ድጎማ ፣ ፍላጎትን ከማናር ፣ ከአቅም በላይ መኖርን ከማጎልበትና አቅም የሌላቸውን ዜጎች ብቻ ሳይሆን አቅም ያላቸውን ጭምር በጅምላ ከመደጎም ወጭ መፍትሔ የሚሰጥ አይደለም። ይህ ደግሞ የመንግስትን ወጪ ያንራል ፣ ልማትን ያኮስሳል ፣ እድገትን ይጻረራል።

- ይከተሉን -Social Media

ምን ይሻላል ? ፈታኙ ጥያቄ ይህ ነው ነማለት ነማሀረበራዊ ትስስር ገጻቸው ያሰፈሩት መረጃ ያመለክታል።
አብዛኛዎቹ ድሃ ሀገራት ዜጎቻቸው እንዳይጎዱ ፣ ነዳጅን ይደጉማሉ ፣ ድጎማ ለነሱ የተለየ ፈተና አይደለም። ሀብታም ሃገራት ግን የዜጎቻቸው የመግዛት አቅም እና አቅርቦት የተሻለ ስለሆነ ነዳጅ ላይ የተለየ ታክስ በመጣል ዋጋውን አንረው ብክነትን እና የአየር ብክለትን ይከላከላሉ።
በጥቅሉ የደሞዝ ጭማሪ የኑሮ ሁኔታን ማሻሻል ካልቻለ ወይም በአጭር ጊዜ አቅርቦትን ማስደግ ፈታኝ ከሆነ ፣ ደሞዝን ከማሳደግ ይልቅ መሰረታዊ አቅርቦቶችን በመደጎም ከሁለቱ መጥፎዎች የተሻለውን መጥፎ መምረጥ ግዴታ ነው። በተለይ፣ ሀገር የድግስ እና የዳንኪራ ቤትነቱን ትቶ ወጭ መቆጠብ ከጀመረ መፍትሔው ሩቅ አይሆንም።

ድጎማንም ሆነ የደሞዝ እድገትን በአንድ ላይ መንፈግ ግን በግሽበት እና በዋጋ ንረት ኑሮው እና ሕይወቱ የሚታመሰውን ሰራተኛ፣ ጡረተኛ፣ በዝቅተኛ ኑሮ ሕይወቱ ፈተና ላይ የወደቀውን ዜጋ ምግብ ሳትበላ ኑር የማለት ያህል ነው። ይህ ደግሞ በመጀመርያ ማህበራዊ ቀውስን በመቀስቀስ ፣ ቀጥሎ ወደ አለመረጋጋት ማምራቱ የማይቀር ነው።

የአለም ገበያ
በአሁኑ ሰአት ዌስት ቴክሳስ መካከለኛ የአንድ በርሜል ድፍድፍ 58 ነጥብ 68 ዶላር እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

የኢኮኖሚ ባለሙያ
አዲስ ማለዳ በጉዳዩ ላይ ያነጋገረቻቸው በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የኢኮኖሚ ባለሙያ ረዳት ፕሮፌሰር አጥላው አለሙ እንደተናገሩት ነዳጅ የትራንስፖርት አንቀሳቃሽ ዋነኛ ጉልበት ነው ነዳጅ ዋጋ መጨመር የማይነካው ዘርፍ አይኖርም።በዚህም ወጪውን ከፍ ያደርገዋል ስለዚህ በነበረው የኑሮ ውድነት ላይ ተጨማሪ ምክንያት ይሆናል ብለዋል።

በዚህም ነዳጅ ሲጨምር በከፍተኛ መጠን ኑሮ ላይ ጫና ይፈጥራል ብለዋል።ምክንያም የትኛውንም አይነት እንቅስቃሴ ለማድረግ ነዳጅ ወሳኝነት አለው አንድ ሰራተኛ ከቦታ ወደ ቦታ ለመንቀሳቀስ የግዴታ ትራንስፖር መጠቀም አለበት ስለዚህ ከሌሎች ወጪቹ በመቀነስ ለትራስፖርት ለማዋል ይገደዳል ይህም ደግሞ ኑሮውን ያጎዳዋል ማለት ነው ሲሉ አስረድተዋል።

ከምርት ጋር በተያያዘ ከክፍለ አገር የሚመጡ ምርቶች ላይ የነዳጅ ዋጋ መጨመሩ ምክንያት የትራንስፖር ጭማሪ ሲደረግ ምርት ላይም ጭማሪ ይኖራል ይህም ኑኖው ላይ ጫና የሚፈጥር አን ምክንየዣት ነው ብለዋል።
መንግስት ድጋፍ አለማድረጉን ተያይዞ መንግስት ከየት ያመጣል ያሉት ፕሮፌሰሩ ሁሉም ነገር ላይ ከመንግስት ድጋፍ መጠበቅ አግባነት የለውም መንግስት ገቢ የሚያገኘው ጀከህብረተሰቡ ነው ነዳጅን ይደግፍ ሌሎች ነገሮች ላይ ጭማሪ ማድረግ ሊኖርበት ነው ብለዋል።
ኢኮኖሚውን ለማስተካከል ሆነ የተሻለ አገር ለመፍተር አምራች ዜን ማፍራት ዋናው እና ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራበት የሚገባ ነው። ሰላም እና መረጋጋትን በማምጣት የሚያወራ ሳይሆን የሚሰራ ትውልድ መፍጠር ይገባናል ሲሉ ያላቸውን ሀሳብ ለአዲስ ማለዳ አስረድተዋል።
የነዳጅ ዋጋ በኹለት ወር ጊዜ ውስጥ ተከታታይ መጨመሩ የእለት ተዕለት እንቅስቃሴው ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖ ቀላል የሚበል አይደለም።የነዳጅ ዋጋ ጭማሪውን እንደ ምክንያት ቆጥረው በትራንስፖርት ላይ በራሳቸው ስልጣን ዋጋ የሚጨምሩ አገልግሎት ሰጪዎች መፍትሄ ሊነበጅላቸው ይገባል።

ቅጽ 2 ቁጥር 119 የካቲት 6 2013

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads
- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች