መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናሕብረት ባንክ የጉዞ ጎ አገልግሎት ክፍያን ለደንበኞቹ ለመቅረብ ከጉዞ ጎ፤ ሶል ጌት...

ሕብረት ባንክ የጉዞ ጎ አገልግሎት ክፍያን ለደንበኞቹ ለመቅረብ ከጉዞ ጎ፤ ሶል ጌት ትራቭል ጋር የጋራ ስምምነት አደረገ

ሕብረት ባንክ ለደንበኞቹ የዲጅታል አውሮፕላን ጉዞ ክፍያ ምርጫን ለማስፋት ከሶል ጌት ትራቭል ጋር የጉዞ ጎ ክፍያ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን አሰራር መዘርጋቱን አስታወቀ፡፡
ይህ አገልግሎት የሕብረት ባንክ ደንበኞች የተለያዩ አየር መንገዶችን ትኬት ግዥ በየትኛውም ጊዜ እና ቦታ በሞባይል ባንኪንግ ወይም ካመቻቸው የሕብረት ባንክ ቅርንጫፍ በመሔድ ክፍያ መፈፀም ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡ ባንኩ አገልግሎቱን ያለምንም ክፍያ ለደንበኞቹ እንደምርጫቸው በሞባይልም ሆነ በቅርንጫፎች በኩል ክፍያ በመፈጸም መጠቀም እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

ይህን ዓይነት አሰራር ሕብረት ባንክ ፈርቀዳጅ ያረገውን ሲስተም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ከስህተት በፀዳ ሁኔታ ላለፉት አራት አመታት የተገበረ መሆኑና አሁንም አገልግሎቱን እየሰጠ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከጉዞ ጎ ጋር የተተገበረው የአየር ቲኬት ክፍያ ሲስተምን ለየት የሚያደርገው የተለያዩ አየር መንገዶችን የበረራ አገልግሎቶች ከነዋጋቸው ጭምር ለደንበኞች በምርጫ በማቅረቡ ነው፡፡

ከወቅቱ ነባራዊ ሁኔታ ብሎም ሕብረት ባንክ ከሚከተለው የዲጂታይዜሽን መርሕ አንፃር እንዲህ ያሉ አገልግሎቶች ለደንበኞች አስፈላጊ እንደሆኑ ባንኩ ይረዳል፡፡ ስለሆነም ጉዞ ጎ፤ ሶል ጌት ትራቭል የጉዞ ጎ አፕልኬሽንን ይዞ በመምጣት ፣ ሕብረት ባንክም የክፍያ ሲስተሙን በመዘረጋት በሁለቱ ተቋማት
መካከል የተደረገው የትብብር ሥራ እና ስምምነት ሊመሰገንና ሊስፋፋ የሚገባው ነው፡፡ ሕብረት ባንክ የFintech ካምፖኒዎችን ያበረታታል፤ ያግዛልም ተብሏል፡፡

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች