ኢትዮጵያ ከሐዋላ 5 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ገቢ አገኘች

0
277

ኢትዮጵያ በ2010 በጀት ዓመት ከሐዋላ 5 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ገቢ መሰብሰቧን ብሔራዊ ባንክ በያዝነው ሳምንት ባወጣው ሪፖርት ገለጸ። ይህ በተመሳሳይ ጊዜ ከተገኘው የውጪ ንግድ ገቢ አንጻር 2 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር ከፍ ይላል።
በተጨማሪም፤ ወደ አገሪቷ በ2010 የገባው የሐዋላ መጠን ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነጻጸር 15ነጥብ7 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን ሪፖርቱ አስነብቧል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ከፍተኛ ለውጥ እያሳየ የመጣው የሐዋላ ገቢ ለብዙ ዓመታት የትይዩ (ጥቁር) ገበያው ጥንካሬ ጋር ተያይዞ ብዙም ጭማሪ ሳያሳይ ቆይቶ ነበር። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከግማሽ በላይ የሆነውን የሐዋላ ገቢ በመሰብሰብ ቀዳሚ ነው።

ቅጽ 1 ቁጥር 9 ጥር 4 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here