ኢትዮጵያ ከ11 ሺህ በላይ ሠራዊት ለዓለም ዐቀፍ የሰላም ግዳጅ አሰማርታለች

0
695

በዓለም ዐቀፍ የሰላም ማስከበር ግዳጅ ላይ 11673 የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት አባላት እንደሚገኙ የመከላከያ ሚኒስቴር የስድስት ወር ሪፖርቱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበበት ወቅት አስታወቀ ። ከ1986 የሩዋንዳ የሰላም ማስከበር ግዳጅ ጀምሮ በተለያዩ አገራት የሰላም ማስከበር ሥራ ሰርቷል። ከእነዚህም ውስጥ በዋናነት በሩዋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ላይቤሪያ፣ ኮትዲቯር፣ አቢዬ፣ ዳርፉር እና ደቡብ ሱዳን ተጠቃሽ ናቸው። የአገር መከላከያ ሠራዊት በዳርፉር፣ በደቡብ ሱዳንና በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ግዳጁን እየተወጣ ይገኛል። ከዚህም በተጨማሪ በቅርቡ በዳርፉርና በአቢዬ በሂደት የሚሰማሩ ተጨማሪ አባላት በሁርሶ ማሰልጠኛ ሥልጠናቸውን ጨርሰው በተጠንቀቅ ላይ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል። ከሰላም ማስከበር የሠራዊት ምደባ ጋር በተያያዘ ሚኒስቴሩ የግማሽ ዓመት ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት ከሠራዊቱ በኩል ቅሬታ እንዳለ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተነስቷል።

ቅጽ 1 ቁጥር 9 ጥር 4 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here