6ኛውን አገራዊ ምርጫ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለማከናወን የለውጥ ሥራዎች መሠራታቸው ተገለጸ

0
596

6ኛውን አገራዊ ምርጫ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለማከናወን በርካታ የለውጥ ሥራዎች መከናወናቸውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታደሠ ጫፎ ገለጹ። አፈ-ጉባኤው ይህንን የገለጹት የስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ ቅድመ ዝግጅት አስመልከቶ ከአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢዎች ጋር በጽሕፈት ቤታቸው በተወያዩበት ወቅት ነው።
ምርጫው ነጻ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች በተሳተፉበት መንገድ የምርጫ ሕጉ መሻሻሉንና የምርጫ ቦርድ አባላት መመረጣቸውን ለታዛቢዎቹ አብራርተዋል።
ምርጫው በተቀመጠለት የጊዜ መርሃ-ግብር እንዲከናወን ለማድረግ የምርጫ ቁሳቁሶች ወደየ ምርጫ ጣቢያዎች እንደተጓጓዙ የጠቀሱት አፈ-ጉባኤው፣ በምርጫው ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት ሕጋዊ አሠራሮችና የጸጥታ አደረጃጀቶች እንደተዘረጉም ነው የተናገሩት።
በጸጥታ ጉዳይ በአንዳንድ የአገሪቷ አካባቢዎች ተራዝሞ የነበረው የመራጮች ምዝገባም በአሁኑ ጊዜ ከሞላ ጎደል መጠናቀቁን የተናገሩት አፈ-ጉባኤ ታደሠ፤ ምርጫው ነጻ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ታዛቢ ቡድኑ በቂ መረጃ ማግኘቱን አረጋግጠዋል። በምርጫው የሴቶችን ተሳትፎ ከፍ ለማድረግና ሴቶች መራጭ ብቻ ሳይሆኑ ተመራጭም እንዲሆኑም መንግሥት በትኩረት ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን የጠቆሙ ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ በአመራር ሰጭነት የሴቶች ተሳትፎ 50 በመቶ መሆኑንም አስረድተዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 131 ሚያዚያ 30 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here