በአዲስ አበባ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ የቴክኒክና ሙያ የልህቀት ማዕከል ሊገነባ ነው

0
696

በአዲስ አበባ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ የቴክኒክና ሙያ የልህቀት ማዕከል ከዓለም ባንክ በተገኘ ከ24 ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ የሚገነባ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ ለማዕከሉ ግንባታ በኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርስቲ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።
ማዕከሉ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለምስራቅ አፍሪካ አገራት አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ የሚገነባ ነው ተብሏል።
ግንባታው የሥልጠና ተደራሽነትን ማስፋት፣ የትምህርትና ሥልጠና ጥራትን ማሻሻል እንዲሁም ቀጠናዊ ትስስርን ማጠናከርን እንደሚያስችል ዶ/ር ሳሙኤል ተናግረዋል።
ማዕከሉ በብረታ ብረት እንዲሁም ቆዳና የቆዳ ውጤቶች ላይ ትኩረት ያደርጋልም ነው የተባለው።
‹‹በቀጣይ 10 አመታት ከምናሳካቸዉ ግቦች መካከል ጥራት ያለዉ የሰዉ ኃይል ማፍራት አንዱ ነዉ›› ያሉት ሚንስትሩ የልህቀት ማዕከሉ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ተጠናቆ ለተማሪዎችና ለሰልጣኞች ጥራት ባለዉ መንገድ ሥልጠና ያቀርባል፤ ለወጣቶች የሥራ እድል ይፍጥራል ብሎም በአካባቢዉ ላሉ ኢንደስትሪዎች ምቹ ሁኔታ ያመቻቻል›› ብለዋል።
የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ አቶ አህመድ መሐመድ ቡህ በበኩላቸዉ የማዕከሉ ግንባታ ለአካባቢዉ እና አጎራባች አገሮች ያለዉን ጠቀሜታ ገልጸዉ ጎን ለጎን የድሬደዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለድሬዳዋ ከተማ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እያበረከተ በመሆኑ ወደ ዩንቨርስቲ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 137 ሠኔ 12 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here