የተከዜ ድልድይ መሰበሩ ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ አስቸጋሪ ሆኗል ተባለ

0
551

ዓለም አቀፍ ተቋማትየድልድዩ መሰበር ሰብዓዊ ድጋፍ የማድረስ ስራውን አስቸጋሪ እንደሚደርገው ተግልጿል። የድልድዩ መሰበር ሰብዓዊ ድጋፍ የማድረስ ስራውን አስቸጋሪእንሚሆን እየተገለጸ ነው።
እንዳባጉናን እና ማይፀምሪ (ልዮ ቀበሌ እምባማድሬ) ከተሞችን የሚያገናኘው የተከዜ ወንዝ ድልድይ መፍረሱን ተረጋግጧል። የአከባቢው ኗሪዎች እንዳሉት ድልድዩ ዛሬ በመሰበሩ አሁን ላይ አገልግሎትእየሰጠ አይደለም። ዓለም አቀፍ የነፍስ አድን ኮሚቴ በይፋዊ የትዊተር ገጹ እንደጻፈው ድልድዩ መፍረሱን አረጋግጧል።
ድልድዩ ዓለም አቀፍ የነፍስ አድን ኮሚቴ ወደ ትግራይ ሰብዓዊ ድጋፎች የሚገቡበት በር እንደነበርም ገልጿል። ድልድዩ በመውደሙ በትግራይ ክልል በተፈጠረው ቀውስ ምክንያት የሰብአዊ አርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ድጋፍ የማድረሱን ስራ እንደሚያስተጓጉለውም ነው የተጠቀሰው።
በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት የደቡብ እና ምስራቅ አፍሪካ ቅርንጫፍ የተከዜ ድልድይ ከጥቅም ውጭ መሆኑን ገልጾ የድልድዩ መሰበር ሰብዓዊ ድጋፍ የማድረስ ስራውን አስቸጋሪ ያደርገዋል ሲል መግለጫ አውጥቷል።
የትግራይ አርሶ አደሮች የመሄር ግብርና እዲያከናውኑ ለመደገፍ የወጣውን የሰብአዊ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ውድቅ ያደረገው የሽብር ቡድኑ ሕወሓት የእርዳታ መስመርን ለመገደብ የተከዜ ድልድይን ሆን ብሎ ማፍረሱን፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ገልጿል።


ቅጽ 3 ቁጥር 139 ሠኔ 26 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here