በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው የተከሰሱት ሶስት ግለሰቦች የጥፋተኝነት ብይን ተላልፎባቸዋል።
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ የጸረ ሽብርና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት የጥፋተኝነት ፍርዱን ያስተላለፈው ሲሆን ጥፋተኛ የተባሉት ገዳዩ ጥላሁን ያሚ እንዲሁም ተባባሪዎቹ ከበደ ገመቹ እና አብዲ አለማየሁ ናቸው፡፡
ችሎቱ የቅጣት አስተያየት ለመቀበል ለሀምሌ 8 ቀን 2013 ተለዋጭ ቀጠሮ መያዙም ታውቋል፡፡



