የ15 አቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ የክረምት በጎ አድራጓት መርሀ-ግብርን በይፋ መጀመሩን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

0
505

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የአቅመ ደካሞችን ቤቶች በማደስ በትምህርት ዘርፉ የሚካሄደውን የክረምት የበጎ አድራጎት መርሀ -ግብርን በይፋ አስጀምረዋል።

በበጎ አድራጎት መርሀ ግብሩም በትምህርት ሚኒስቴር ድጋፍ በክፍለ ከተማው 15 የአቅመ ደካሞች ቤት እንደሚታደስም ተገልጿል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ) የኢትዬጵያዊነት መገለጫ የሆነው የመተጋገዝ እና የመደጋገፍ ባህልን መሰረት በማድረግ የአቅመ ደካሞችን ቤት ማደስ በመቻላችን ደስታ ይሰማናል ብለዋል።

በሁለት ሳምንት ውስጥም ቤቶቹ ታድሰው ለነዋሪዎቹ እንደሚያስረክቡም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ለአቅመ ደካሞቹም ቤቱን ከማደስ ባሻገር አስፈላጊ የቤት እቃዎችም እንደሚሟሉ ተገልጿል።

ከዚህም ጋር በተያያዘ ተማሪዎች በክረምቱ መርሀ-ግብር በየአካባቢያቸው በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች በመሳተፍ ከወገን አልፈው ሀገርን የማገዝ ሀላፊነታቸውን በንቃት እንዲወጡ ሚኒስትሩ ጥሪ ማቅረባቸውን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here