የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ወጣቶች በሰላም እና አካባቢ ጥበቃ የልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበት ሴሚናር ተጀመረ

0
1151

የሰላም ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ወጣቶች በሰላም እና አካባቢ ጥበቃ የልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበት ሴሚናር መጀመሩን ይፋ አድርገዋል።

ዛሬ በአዲስ አበባ የተጀመረው ከ10 የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ወጣቶች በሰላምና በአካባቢ ጥበቃ ያላቸውን ተሳትፎ በሚያጎለብቱበትና ልምድ የሚለዋወጡበት ብሎም በሀገራቱ ላይ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን በሚደረጉ ጥረቶች ሚናቸውን እንዲወጡ የማስቻል ዓላማ ያለው ሴሚናር መሆኑ ተገልጿል።

አፍሪካ የወጣቶች አህጉር እንደመሆኗ መጠን ወጣቶች ሰላምን በመጠበቅና በመንከባከብ ብቻ ሳይሆን አዎንታዊ ሰላምን እንዴት ማምጣት ይችላሉ የሚለውን ፀንሰ-ሐሳብ በጥልቀት እንዲመለከቱ በር የሚከፍት ፕሮግራም መሆኑም ተገልጿል።

የምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀነራል ጌታቸው ሽፈራው በበኩላቸው ወጣቶች በቀጠናው ሰላምን በማስፈን እና በአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ላይ ተግባራዊ ተሳትፎ ለማድረግ የሚችሉበትን የጋራ ዓላማ አንግበው እንዲንቀሳቀሱ ለማድረግ የሚያስችል መድረክ መሆኑን አመልክተዋል።

በሴሚናሩ የሁለተኛው ቀን ፕሮግራም ድንበር የለሽ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት መጀመርን ይፋ በማድረግ በእንጦጦ ፓርክ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም እንደሚከናወን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

 

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here