የቻይና ትያንጂን ማይወይ ኢንተርናሽናል የተሰኘ የግል ካምፓኒ ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የፈንጅ ማምከኛ መሳሪያዎችን ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል፡፡
ኩባንያው በ22 ሚሊየን 8 መቶ ሰማኒያ ሺህ ብር የሚገመቱ የፈንጅ ማምከኛ መሳሪያዎችን በዛሬው እለት ለፌዴራል ፖሊስ በድጋፍ አበርክቷል፡፡
በአሁኑ ወቅት ተቋሙ ለፀረ-ፈንጅ ባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት በተለያዩ መሰረተ ልማቶች እና ትላልቅ ተቋማት ላይ በማሰማራት በዘመናዊ መሳሪያዎች የተደገፈ ፖሊሳዊ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ከፈንጅ ማምከኛ መሳሪያዎቹ በተጨማሪ በሰለጠኑ የፈንጅ አነፍናፊ ውሾች በመታገዝ ከፀረ-ፈንጅ ባለሙያዎች የተሰወሩ ነገሮችን የመለየት ስራ እንደሚሰራም ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገነኘው መረጃ ያመላክታል።
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ በመገኘት ባደረጉት ንግግር የፀረ-ፈንጅ መሳሪያዎቹ የፀረ-ሰላም ኃይሎችን እኩይ ተግባር ለመመከት እጅግ አስፈላጊ መሆናቸውን በመግለፅ ካማፓኒው ላበረከተው ድጋፍ በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የፀረ-ፈንጅ ምክትል ዳይሬክቶሬትም መሳሪያዎቹን በአግባቡ በመጠቀም ለተፈለጉለት አላማ እንዲያውላቸው ኮሚሽነር ጄነራሉ ከአዳራ ጭምር አሳስበዋል፡፡





