የፌደራል መንግሥት የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ ለሚሹ ሁሉም አካል ወደ ትግራይ በረራ እንዲያደርጉ መፍቀዱን አስታወቋል።
የአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ማጣሪያ በትዊተር ገጹ ይፋ እንዳደረገው የፌደራል መንግሥት ወደ ትግራይ የሚደረጉ በረራዎችን ከሰኞ ሰኔ 28/ 2013 ዓ.ም ጀምሮ ፍቃድ መሰጠቱን አስታወቀ።
መንግሥት የተናጠል የተኩስ አቁም ማወጁን ተከትሎ የህወሓት የጥፋት ኃይሎች በተመሳሳይ የተኩስ አቁም ለማድረግ ባለ ሰባት ነጥብ ቅድመ ሁኔታዎችን ባለፈው ዕሁድ ለፌደራሉ መንግሥቱ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው። ከእነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች መካከል “ያለ ቅድመ ሁኔታ ዓለም አቀፍ በረራዎች በትግራይ ወደሚገኙ አየር ማረፊያዎች የቀጥታ ጉዞ እንዲያደርጉ መፈቀድ” የሚል ይገኝበታል።
ይህንንም ተከትሎ የፌደራል መንግሥት የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ ለሚሹ አካልት ወደ ትግራይ በረራ እንዲያደርጉ መፍቀዱ ተገልጿል።
ይሁን እንጂ ይህ ፍቃድ፤ ከዓለም አቀፍ መነሻዎች በቀጥታ ወደ ትግራይ ለሚደረጉ የቀጥታ በረራዎች ይሁን አልያም በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ከሚገኙ የአየር ማረፊያዎች ወደ ትግራይ ክልል ስለሚደረጉ በረራዎች ስለመሆኑ የአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ማጣሪያ በግልፅ ያስቀመጠው ነገር የለም።




