ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተማሪዎች ጋር በመሆን በጉለሌ እፀዋት ማዕከል የአረንጓዴ አሻራ ችግኞችን ተከሉ

0
1111

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተማሪዎች ጋር በመሆን በጉለሌ እፅዋት ማዕከል የአረንጓዴ አሻራ ችግኞችን ተከሉ።

“የሀገር ተረካቢነታችንን በአረንጓዴ አሻራችን ኢትዮጵያንችንን እናልብስ” በሚል ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ከ30ሺህ በላይ ተማሪዎች፣ መምህራን እና የትምህርት ማህበረሰብ አመራሮች ችግኞችን መትከላቸው ታውቋል።

ተማሪ እያለን ሰኔ 30 ዓመቱን ሙሉ የተማርነውን ውጤት ለማወቅ በጉጉት የምንጠብቀው ቀን ነው ያሉት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ዛሬ ደግሞ ተማሪዎች ኢትዮጵያን እናልብሳት በማለት ችግኝ በመትከል አሻራ ማኖራቸውን ገልጸዋል::

ዛሬ የተተከሉ ችግኞችም ለነገይቱ ኢትዮጵያ እና ለአዲስ አበባ ልምላሜ የተላበሰች ፣ ለኑሮ የተመቸች እንድትሆን የሚያደርግ በመሆኑ ተማሪዎች ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን መከትኮት እና መንከባከብ ይገባቡ ሲሉ ምክትል ከንቲባዋ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በዛሬው ዕለት በከተማዋ በሁሉም የመንግሥት እና የግል ትምህርት ቤቶች በአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐግብር ከ100ሺህ በላይ ችግኞች እንደሚተኩ የአዲስ አበባ ከተማ ትምሀርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ መግለጻቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here