በመዲናዋ ሀሰተኛ ብር ሲያትሙ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

0
670
በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ሀሰተኛ ብር ሲያትሙ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡
በክፍለ ከተማው ሀሰተኛ ብር በማተም በሀገሪቱ ኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ፣ ፀጥታና ደህንነት ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ ቡድኖችና ግለሰቦችን ለአንድ ወር ያህል የመረጃና ክትትል ሥራ ሲሰራ መቆየቱ ተገልጿል፡፡
በዚህም ትናንት ምሽት የሀሰተኛ ብር አታሚዎች ከእነ ሀሰተኛ ብር ኖቶች፣ ማተሚያ ማሽኑ እንዲሁም ከተባባሪዎቹ ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል ።
ምክትል ከንቲባዋ በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ክትትል በማድረግ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር እንዲዉሉ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here