ኢትዮጵያ እና ሜክሲኮ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተወያዩ

0
558

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከሜክሲኮ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርሴሎ ኢብራርድ.ጋር በበይነ መረብ ውይይት አድርገዋል።

በውይይታቸው ወቅት በሁለቱ ሀገት መካከል የቆየውን የሁለትዮሽ ግንኙነት የተመለከቱ ሲሆን ይህም ግንኙነት የበለጠ መጠናከር እንዳለበት አንስተዋል፡፡

በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ እየተካሄደ ባለው የሶስትዮሽ ድርድር ላይም ተወያይተው በአፍሪካ ህብረት መሪነት በቅን ልቦና በመወያየት እርቀ ሰላም የመምጣቱ አስፈላጊነት ላይም ተነጋግረዋል፡፡

በተጨማሪም አቶ ደመቀ በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታዎችን በተለይም በትግራይ ክልል ተፈፀሙ የተባሉ የሰብዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮምሽንና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ተቋም የጋራ ምርመራ እያከናወኑ መሆኑን ገልፀው፣ ይህንን አዎንታዊ እርምጃ ከግምት ያላስገባ ጫና ግን ተቀባይነት የሌለው ነው በማለት አስረድተዋል።

ሚስተር ማርሴሎ ኢብራርድ በመጨረሻ በሀገሪቱ ወቅታዊ ወሳኝ ጉዳዮችን አስመልክቶ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሰጡት መግለጫ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል ፡፡

በተጨማሪም በትግራይ የኢትዮጵያ መንግስት ያወጀው የአንድ ወገን ሰብአዊ የተኩስ አቁም የሚያስመሰግን እና መንግስት ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here