በምዕራብ ኦሮሚያ 3 ዞኖች የሚገኙ 18 የንግድ ባንኮች ተዘረፉ

0
778

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች በሚገኙ 18 የንገድ ባንኮች መዘረፋቸውን ክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ጥር 7/2011 ባወጣው መግለጫ አመልከቷል።
ዝርፊያውም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ላይ ስለመፈጸሙ ጠነገረ ሲሆን ምን ያህል ገንዘብ እንደተወሰደ የተባለ ነገር የለም።
ዝርፊያው ከባንክ አልፎ በኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ ተቋም ላይ የተፈጸመም ሲሆን በግልና የመንግሥት ንብረቶች ላይ ውድመት መድረሱንም ቢሮው አሳውቋል። ከመንግሥት መስሪያ ቤቶችና ሰነዶች ቃጠሎ ባለፈም 10 የመንግሥትና የግል ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል ተብሏል።
ጥፋቱን ያደረሱት እነማን እንደሆኑ ግልጽ ያላደረገው ቢሮው ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር እያዋለ እንደሆነ አሳውቋል። ነዋሪዎችና አንዳንድ የመንግሥት ኃላፊዎች ለጥፋቱ ኦነግን ተጠያቂ ሲያደርጉ፣ ኦነግ በበኩሉ ዝርፊያ አልፈጸምኩም ብሏል።
በተያያዘ በምዕራብ ኢትዮጵያ ሕገ ወጥ ትጥቅ ታጥቀው የሕዝቡን ሰላም ሲያውኩ ነበር የተባሉ 835 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ስለማዋሉ የምዕራብ ኢትዮጵያ ኮማንድ ፖስት አስታውቋል።
በሌላ ዜና በደቡብ ዞን የኦነግ ጦር የጉጂ ኦሮሞ አባ ገዳዎች ያቀረቡለትን የሰላም ጥሪ መቀበሉን ያመለከተው የቢሮው መግለጫ በኤሊያስ ጋምቤላ ጎሎ የሚመራው የጉጂ ዞን የኦነግ ጦር ሰላማዊ ትግል ወደ ማረፊያ እየገባ መሆኑንም አክሏል።

ቅጽ 1 ቁጥር 10 ጥር 11 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here