አምባሳደር ወይንሸት ታደሰ የሹመት ደብዳቤያቸውን አቀረቡ

0
818

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ወይንሸት ታደሰ ለዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት ፍሌክስ ትሽኪዴ የሹመት ደብዳቤያቸውን አቅርበዋል።

በወቅቱም አምባሳደር ወይንሸት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ጉዳይ ዙሪያ ከፕሬዝዳንቱ ጋር ውይይት ማድረጋቸው ታውቋል።

በተጫማሪም ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን አስመልክቶ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በተደረገው ውይይት ወቅት በዲሞክራቲክ ዲፐብሊክ ኮንጎ በኩል ለቀረበው ገንቢ ንግግር ለፕሬዝዳንቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ኢትዮጵያና ኮንጎ ረጅም ዓመታት የቆየ ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው አገራት ሲሆኑ የኤምባሲው ዳግም መከፈትም ግንኙነቱን ይበለጠ ለማጠናከር ያስችላል ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here