የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የዘንድሮው የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በዛሬው ዕለት ችግኝ በመትከል ተጀምሯል፡፡
ባለስልጣኑ በዛሬው ዕለት አመራሮችን፣ሰራተኞችን እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር ከቁስቋም -እንጦጦ ማሪያም በሚገኘው የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በግራና በቀኝ ባሉ ክፍት ቦታዎች ላይ ሁለት ሺ ችግኞችን የመትከል ስራ በይፋ አስጀምሯል፡፡
በችግኝ ተከላ መርሀ ግብሩ ላይ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መገስ ጥበቡ እንደገለፁት በተያዘው የክረምት ወራት የ 30 ሺ ችግኞች ተከላን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ የበጎ አድራጎት ስራዎች ይከናወናሉ ብለዋል፡፡
ኢንጂነር ሞገስ አክለውም በክረምቱ ወራት 15 የሚሆኑ የአቅመ ደካማ ቤቶችን የማደስ ፣ በተመረጡ ሆስፒታሎች እና ትምህርት ቤቶች የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ጥገና ስራዎች እና 50 ለሚሆኑ ችግረኛ ህፃናት ድጋፍ ይደረጋል ማለታቸውን ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡






