የኦሮሚያ ክልል ለ2014 በጀት ዓመት 124 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት ማዘጋጀቱን አስታወቀ

0
833

የኦሮሚያ ክልል ለ2014 በጀት ዓመት 124 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት ማዘጋጀቱን የጨፌ ኦሮሚያ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ አስታወቀዋል።

አፈ ጉባኤዋ ሀምሌ 9 እና 10 የሚካሄደውን የጨፌውን መደበኛ ጉባኤ አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

ምክር ቤቱ በ14 መደበኛ፣ 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን፣ 6ኛ ዓመት ጉባኤው የ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት ተጨማሪ በጀት ማጽደቅን ጨምሮ 11 አጀንዳዎች ላይ ውይይት ያደርጋል ተብሏል።

አፈ ጉባኤዋ በመግለጫቸው በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት በአብዛኛው ለካፒታል ስራ የዋለ የ14 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ረቂቅ በጀት እንደሚያፀድቅ አስታውቀዋል።

ኦሮሚያ ክልል በዚህ ዓመት ከ11 ሺህ በላይ ፕሮጀክቶችን ለመጨረስ ከፍተኛ ወጪ ማውጣቱና በዋጋ ግሽበቱ ምክንያት ተጨማሪ በጀት ማስፈለጉን ገልጸዋል።

ከዚህ ባለፈም የመንግስት የተለያዩ ዘርፎች እቅድ ክንውን የሚቀርብ ሲሆን የቀጣይ ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይም ውይይት ይደረጋል ብለዋል።

ከአዋጆች አንጻርም ባህላዊ ፍርድ ቤቶችን ከመደበኛ ፍርድ ቤቶች ጎን ለጎን እንዲሰሩ የሚያስችል አዋጅ ይጸድቃል ነው ያሉት።

ለ2014 በጀት ዓመት ለክልሉ 124 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት መዘጋጀቱን ጠቅሰው ለጨፌ ኦሮሚያ ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።

በጀቱ በተመሳሳይ ክልሉ ለሚያከናውናቸው የካፒታል ስራዎች እንደሚውልም አፈ ጉባኤዋ ግልፀዋል።

ጨፌ ኦሮሚያ በ2013 በጀት ዓመት 10 አዋጆችንና 5 ደንቦችን አጽድቆ የህዝቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማሳደግ መቻሉንም አስታውሰዋል።

የክልሉ ምክር ቤት አባላት በምርጫ ዙሪያ፣ በኮቪድ 19ና በሕብረተሰብ ተሳትፎ የሚሰሩ ስራዎች ላይ ብዙ መልካም ነገሮችን ማከናወኑንም ገልጸዋል።

የምክር ቤቱ አባላት በነገው እለት ምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ 3 ሺህ ችግኞችን ለመትከል መዘገጀታቸው ተገልጿል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

 

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here