“ግብር ከፋዮች ትክክለኛ ስልክ አለማስመዝገባቸው ችግር ሆኖብኛል”:- የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

0
803

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ግብር ከፋዮች ትክክለኛ ስልክ አለማስመዝገባቸው ችግር እንደሆነበት አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የ2013 ዓ.ም “የደረጃ ሐ” የገቢ ግብር ከፋዮችን ለማስተናገድ አጭር የጽሁፍ መልዕክት እንዲደርሳቸው በማድረግና ግብራቸውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል እንዲከፍሉ የጀመርኩት አሰራር ፤ግብር ከፋዮች ትክክለኛ ስልክ አለማስመዝገባቸው እንቅፋት ሆኖብኛል ሲል ገልጿል፡፡

ከአጭር የጽሁፍ መልዕክት ውጪ የኔትዎርክ መቆራረጥም ተጨማሪ እንቅፋት እንደሆነ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የታክስ ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ረታ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ግብር ከፋዮች በ7075 አጭር የጽሁፍ መልዕክት ሲደርሳቸው የተላከላቸውን የግብር መጠን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመክፈል ክሊራንስ እንዲወስዱ የተጀመረ አሰራር እንዳለ ተናግረው፣ ወረዳዎች የሚገኙበት ቦታ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት አለመኖር ለአሰራሩ ችግር እንደፈጠረባቸውም አብራርተዋል አቶ ተስፋዬ።

ይህን ችግር ለመቅረፍም ከኢትዮ ቴሌኮም ከመብራት ሀይልና ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ጋር እየሰራን ነው ብለዋል።

በአዲስ አበባ ሶስት መቶ ሺ የሚደርሱ የደረጃ ሐ ግብር ከፋዮች መኖራቸው የተገለጸ ሲሆን ለ164ሺህ የግብር ከፋዮች ውሳኔ መሰጠቱም ተገልጿል።

ከነዚህም ውስጥ ለ106 ሺ 695 ግብር ከፋዮች የአጭር የጽሁፍ መልዕክት እንደደረሳቸው ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያሳያል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here