በህዳሴው ግድብ ላይ የሚደረገው የሚኒስትሮች ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

Views: 205

የኢትዮጵያ፣ የግብጽ እና የሱዳን የውሃ ሚኒስትሮች በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚያካሂዱት የቴክኒክ ስብሰባ የአለም ባንክ እና አሜሪካ ታዛቢዎች በተገኙበት አራት ሰአት ላይ በስካይ ላይት ሆቴል ዛሬ አርብ ህዳር 5 2012 ተጀመረ፡፡

የኢትዮጵያ የውሃ የመስኖ እና የኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ስለሺ በቀለ(ዶ/ር) በትዊተር ገፃቸው እንደገለፁት የሶስቱም ሃገራት ተወካዮች በስፍራው የተገኙ ሲሆን ታዛቢዎችንም እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል፡፡

የሦስቱ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሮች በግድቡ ዙሪያ በአሜሪካ እና የዓለም ባንክ አወያይነት በዋሽንግተን ዲሲ ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል። በውይይቱ ላይ በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ እና ውሃ አሞላል ዙሪያ በኹለት ወራት ውስጥ መስማማት ካልቻሉ ሦስተኛ ወገን እንዲያደራድራቸው ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር።

በተመሳሳይ ሦስቱ አገራት ባወጡት የጋራ መግለጫ የውሃ ሚኒስቴሮቻቸው ከዚህ በኋላ በሚያደርጉት ውይይት ላይ ዓለም ባንክ እና አሜሪካ በታዛቢነት እንዲሳተፉ ተስማምተው ነበር።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com