“ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆችም እንኩዋን ደስ አላችሁ:” ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ

0
449

የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ዛሬ በትዊተር ገፃቸው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት መጠናቀቅን አስመልክተው የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

ሚኒስትሩ እንዳሉት “የሁለተኛውን አመት የህዳሴ ግድብ ሙሌት ተገባዶ ውሃው በግድቡ አናት ላይ ፈሷል::”

“ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆችም እንኩዋን ደስ አላችሁ: ይህ ውጤት ማለት 2 ተርባይኖችን ለማንቀሳቀስ የሚያስፈልገውን የውሃ መጠንና ይዘናል ማለት ነው::”

“በዘንድሮው አመት እየዘነበ ያለው ውሃ መጠን እጅግ ከፍተኛ ነው: ይህም ከፈጣሪ የተሰጠን ፀጋ ምን ያህል ትልቅ እንደሆነና እንዴት እያገዘን እንደሆነ መረዳት እንችላለን ለዚሁም ምስጋና ይግባው::”

“እዚህ ደረጃ ለመድረስ በዘንድሮው አመት መጠነ ሰፊ ስራ ሰርተናል:: በቀጣይ ሁለቱ ተርባይኖች እንዲያመነጩ ብርቱ ስራዎች እየተሰሩ ነው እናም ያንን በቅርብ ወራት በማጠናቀቅ ልፋታችንን ውጤት ላይ እናደርሳለን:: “ በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here