የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ በማይ ዓይኒ እና ዓዲ ሓሩሽ መጠለያዎች የሚገኙትን ኤርትራውያን ስደተኞች በከፊል በድጋፍ ላይ በተመሰረተ የከተማ ስደተኝነት ተጠቃሚ ለማድረግ ማቀዱ የሚበረታታ መሆኑን ገለጸ።
ኮሚሽኑ የዕቅዱ መተግበር ስደተኞቹ በግጭት ምክንያት የተጋረጠባቸው የደህነት እን እርዳታ በበቂ ሁኔታ ያለማግኘት ስጋትን ከማቃለሉም በተጨማሪ ኢትዮጵያ ቀስ በቀስ ስደተኞችን ከካምፖች ውጪ ለማኖር የገባችውን ቃል ለመፈጸም አዎንታዊ እርምጃ ነው ብሏል።
የተ.መ.ድ. የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽንን ጨምሮ በስደተኛ ጉዳይ ላይ የሚሰሩ አለም አቀፍ እን አገራዊ ድርጅቶች እና ለጋሾች ይህንን እቅድ እንዲተገበር በኩላቸውን አስተጾ እንዲያደርጉም ኮሚሽኑ ጥሪውን አቅርቧል።




