ህወሃት ጨቅላ ህጻናትን ለጦርነት መማገዱን አጥብቀው እንደሚቃወሙ የወላይታ ዞን ሴቶች ገለጹ

0
997

በኢትዮጵያ መንግስት በአሸባሪነት የተፈረጀው የህወሃት ቡድን ጨቅላ ህጻናትን ለጦርነት መማገዱን አጥብቀው እንደሚቃወሙ የወላይታ ዞን ሴቶች ገለጹ።

የዞኑ ሴቶች ከሁለት ሚሊየን ብር በላይ በመሰብሰብና ስንቅ በማዘጋጀት ከጀግናው መከላከያ ሠራዊት ጎን መቆማቸውን የወላይታ ዞን ሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳይ መምሪያ አስታውቋል።

ለሀገር ሠላምና ሉዓላዊነት ቅድሚያ የምንሰጥ ህዝብ በመሆናችን ሴት ወንድ ሳንል የተቃጣብንን ትንኮሳ ለመመከት የሚዋደቀውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት የመደገፍና ሌሎችንም የሀገር ልማቶች ለማስቀጠል ያለንን አቅም አሟጠን በመጠቀም እንደግፋለን ያሉት የወላይታ ዞን ሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ጸጋ ፋንታ ናቸው።

የዞኑ ሴቶች በዓይነትና በገንዘብ እንዲሁም ስንቅ በማዘጋጀት የሚቀጥሉ መሆናቸውን በመግለጽ ለዚህም ከሁለት ሚሊየን ብር በላይ በመሰብሰብ በድጋፋቸው ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጎን መቆማቸውን ኃላፊዋ ተናግረዋል።

የወላይታ እናቶች ከምንም በላይ ለሰላም ቅድሚያ እንደሚሰጡ ነገር ግን በህወሃት የተቃጣውን ትንኮሳና ጥቃት ለመመከት ለሀገር አንድነት ውድ ሕይወቱን እየከፈለ ካለው መከላከያ ሠራዊት ጎን በመቆም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ መግለፃቸውን ከዞኑ የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ህወሃት ሕጻናትን ለትምህርት እንጂ ለጦርነት በመመልመሉ የፈጸመው ወንጀል የአሸባሪነቱን ጥግ የሚያሳይ መሆኑንም ነው ያሰረዱት።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here