የሳዉዲ አረቢያዉ ግዙፉ የነዳጅ አምራች ኩባንያ ሳዉዲ አራምኮ (Saudi Aramco) የሾለከበትን ሚስጥራዊ መረጃ ለማስጠፋት 50 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ክፍያ በዲጂታል ገንዘብ እንዲፈጽም መጠየቁን አስታወቀ።
በኩባንያዉ የሶስተኛ ወገን ኮንትራክተር ላይ በደረሰ የሚስጥራዊ መረጃ ማፈትለክ አደጋ ጋር በተያያዘ ችግሩ መከሰቱ ተጠቁሟል።
“ሳዉዲ አራምኮ” አደጋዉ መከሰቱን ያወቀዉ ከኩባንያዉ ጋር የተያያዙ ጥቂት መረጃዎች በኦንላይን መታየታቸዉን ተከትሎ ኩባንያዉ ጥቃቱን ይፋ ማድረጉን አሶሼትድ ፕረስ ገልጿል።
ሆኖም መረጃው የሾለከዉ በኮምፒዉተር ስርአቶቻችን ላይ በተፈጸመ ጥቃት ምክንያት አይደለም ያለዉ “ሳዉዲ አራምኮ” በስራቸው ላይ ምንም ተጽኖ አለመፍጠሩን ጨምሮ ገልጿል።
በሳይበር ወንጀለኞች እጅ የገባዉ የኩባንያዉ መረጃ አንድ ቴራባይት( አንድ ሚሊዮን ሜጋ ባይት) መጠን ያለው መሆኑንም አሶሼትድ ፕረስ በድረ-ገጹ አስፍሯል።



