የሱማሌ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው የ5ኛ ዓመት 13ኛው መደበኛ ጉባኤ የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ አዋጅ ማጽደቁን የክልሉ የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ገለጸ።
የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ዳይሬክተር አቶ አብዱልከሪም አህመድ፣ የክልሉ ምክር ቤት አባላት በቀረበላቸው የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት በማድረግ አጽድቀዋል ብለዋል፡፡
ምክር ቤቱ የሀብት ምዝገባ አዋጁን ከማጽደቁም በተጨማሪ የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅን በማሻሻል በክልሉ የተለያዩ መስሪያ ቤቶች ውስጥ የሚገኙ የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች ተጠሪነታቸው ለክልሉ የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን እንዲሆን መወሰኑንም አቶ አብዱልከሪም ገልጸዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ አገራዊ የሥነ-ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ሥራዎችን ምሉዕ ለማድረግና አገራዊ መልክ ለማስያዝ የአዋጁ መጽደቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ከፌደራል የሥነ-ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ቅጽ 3 ቁጥር 142 ሐምሌ 17 2013


