ወደ ኢትዮጵያ ገብተው ከነበሩ 560 ሶሪያዊያን መካከል 395 የሚሆኑትን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እንዳደረገ የኢሚግሬሽን፣ የዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አስታወቀ።
ከሰባት ዓመታት በላይ በእርስ በእርስ ጦርነት ተዘፍቃ በምትገኘው ሶሪያ ከኅልፈት የዳኑ ዜጎቿ ወደተለያዩ አገራ እየተሰደዱ ነው። ወደ ኢትጵያ ከመጡትም አብዛኛዎቹ ዜጎች በጎብንትና ትራንዚት ቪዛ የገቡ ሲሆኑ በልመና ላይ ተሰማርተው እንደነበር ይታወሳል።
ዜጎቹ በአዲስ አበባ በሚገኙ ትላልቅ ሆቴሎች፣ የብዙኃን ትራንስፖርትን ጨምሮ ሰው በሚበዛባቸው ስፍራዎችና አውራ ጎዳናዎች ላይ ለልመና እጃቸውን ሲዘረጉ ስለመክረማቸው ኤጀንሲው አስታውቋል።
ከአዲስ አበባ ውጭም በሐዋሳ በልመና ላይ የተሰማሩ የሶሪያ ዜጎች መበራከታቸውን ተቋሙ ገልጿል። ኢትየጵያ አሁን ላይ ከ800 ሺህ በላይ ስደተኞችን ተቀብላ የማኅበራዊ አገልግሎት እንዲያገኙ እያደረገች ትገኛለች።
ቅጽ 1 ቁጥር 11 ጥር 18 ቀን 2011



