በጥረት ኮርፖሬት ሀብት በማባከን ወንጀል ተጠርጥረው ጥር 15 በአማራ ክልል መንግሥት በቁጥጥር ስር የዋሉት በረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ ያቀረቡት የወስትና ጥያቄ ውድቅ ሆነ።
ትናንት በባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ጉዳያቸው መታየት ከጀመረው ኹለቱ ተጠርጣሪዎች ውስጥ በረከት በጥረት ኮርፖሬት ኩባያዎች ጠፍቷል ለተባለው ገንዘብ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ በውጭ ሆነው እንዲከራከሩ ጠይቀዋል። በባሕር ዳር ለሕይወታቸው እንደሚሰጉና የጤና ችግርም ስላባቸው ጉዳያቸው አዲስ አበባ እንዲታይላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል። ታደሰም በተመሳሳይ ጉዳያቸው አዲስ አበባ እንዲታይና በዋስ ወጥተው በውጭ እንዲከራከሩ ጠይቀዋል። በመገናኛ ብዙኃን የሥም ማጥፋት ዘመቻ እየተፈጸመብን ነው ሲሉም ተጠርጣሪዎቹ አቤት ብለዋል።
ግለሰቦቹ የተጠረጠሩት በከፍተኛ ገንዘብ ነው ያለው አቃቤ ሕግ በበከሉሉ የቀደመ ሥልጣናቸውን ተጠቅመው መረጃ ይሰውሩብኝል በሚልም የዋስ መብት እነዳያገኙ ጠይቋል።
የዋስትና ጥያቄውን ወድቅ ያደረገው ፍርድ ቤቱ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜን በመፍቀድ ለየካቲት 1 ቀጠሮ ሰጥቷል።
ቅጽ 1 ቁጥር 11 ጥር 18 ቀን 2011