ኢትዮጵያና ስዊዘርላንድ ተደራራቢ ግብርን ለማስቀረት ስምምነት ተፈራረሙ

0
813

ኢትዮጵያና ስዊዘርላንድ በመካከላቸው ያለውን ተደራራቢ ግብር ለማስወገድ የሚያስችል ስምምነት መፈራረማቸው ታወቀ።
ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ እና በኢትዮጵያ የስዊዘርላንድ አምባሳደር ታማራ ሞና ተፈራርመውታል።
ስምምነቱ የስዊዘርላንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ሀብታቸውን በልማት ሥራ ላይ እንዲያውሉ ለማበረታታትና የኢትዮጵያም ባለሀብቶች በስዊዘርላድ ገበያ ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ለማስቻል ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ተደራራቢ ግብር ለውጭ ኢንቨስትመንት ማነቆ በመሆኑ ከስዊዘርላንድ መንግሥት ጋር ሦስት ዙር ድርድር በማድረግ የተደራራቢ ግብርን ለማስወገድ መግባት ላይ መደረሱም ነው የተገለጸው።
ከፊርማ ሥነ-ስርአቱ በኋላ የኹለቱን አገራት ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ መምከራቸውን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተገኘነው መረጃ ያመላክታል።


ቅጽ 3 ቁጥር 143 ሐምሌ 24 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here