ሴቶችና ጭንቀት

0
799

“ሲቄ” የሚለው የኦሮምኛ ቃል ‹አለንጋ› የሚል ትርጉም አለው። በገዳ ትውፊታዊ አስተዳደር ውስጥ በባሏ ጥቃት የደረሰባት ሚስት፣ ከሌሎች ሴቶች ጋር በመሆን ባሏ ላይ የካሣ ውሳኔ የምታሳልፍበት ስርዓት ሲቄ ይባላል።

ተማሪ ሳሮን አሰፋ የዩንቨርስቲ ተማሪ ስትሆን፣ ጭንቀትን እንዲህ ስትል ትገልጻዋለች፤ ጭንቀት በብዙ መንገድ ሊመጣ የሚችል የመንፈስ መረበሽ ነው። አውቃም ሆነ ሳታውቅ የምትጨነቅበትን ሐሳብ እንደ ጭንቀት ታየዋለች። በብዙ በማታውቃቸው ጉዳዮች ላይ እንደምትጨነቅም ትናገራለች ።

የቤተሰብ ሠላም መሆን፣ የትምህርት ማጠናቀቅና በቀጣይ ስለሚገጥማት የሥራ ዕድል ሳሮን ከምትጨነቅባቸው ሐሳቦች መካከል እንደ ምሳሌ የምታነሳቸው ናቸው። ከዚህም ጋር በተያያዘ ለእራስ ምታትና ከፍተኛ ለሆነ ድብርት እንደምትጋለጥ እና በፈተና ወቅት ተረጋግታ ባለመሥራተዋ በትምህርቷ ያሰበችውን ውጤት ማምጣት እንዳልቻለች ትናገራለች።

ጭንቀት ተማሪዎችን ብቻ ሳይሆን ሴት ሠራተኞችንም በይበልጥ ይፈትናል። ለዚህም እንደ ማሳያ የምትሆነን የውብዳር መኮንን ናት። የግል ሠራተኛ ስትሆን ጭንቀት ለሷ መጥፎ የሚባል በሽታ እንደሆነ ትናገራለች። የውብዳር አሁን ያለው የአገሪትዋ ወቅታዊ ሁኔታ ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ አንደከተታት ታስረዳለች።

ከዚህም በተጨማረ በአገሪትዋ ላይ ከዕለት ወደ ዕለት በፈጣን ሁኔታ እየጨመረ በመጣው የኑሮ ውድነት ምክንያት ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ መግባትዋን ታነሳለች።
የብዙ ቤተሰብ አስተዳዳሪና የ 3 ልጆች እናት የሆኑት ብርሃኔ ተረፈ ኑሮ በከፈተኛ ሀኔታ በመጨመሩ የሚያስፈልጋቸውን ነገር ማሟላት እንዳልቻሉ ይጠቁማሉ። የልጆች እናት መሆናቸው ሁኔታው በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አድርጎታል።
በአጠቃላይ ኹሉም ሴቶች ጭንቀት በማንኛውም ሁኔታ ሊከሰት የሚችል በመሆኑ ራስን ከጭንቀት መከላከል እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።

ብዙ ሴቶች ያጋጠማቸው ጭንቀት እንደሚፈታ ቢያስቡም የሚፈታበትን መንገድ አለማወቃቸው ግን ሁኔታውን ይበልጥ ያከብደዋል። ይልቁንም ጭንቀት ውስጥ በሚገቡበት ወቅት ከሰው መነጠል፣ መተኛትና ማልቀስ ይመርጣሉ። ይህ አይነቱ ድርጊት ይበልጥ በገቡት ሐሳብ ውስጥ ረጅም ጊዜን እንዲያሳልፉ ያደርጋቸዋል።

ሴቶች የሚያስጨንቅ ጉዳይ በሚያጋጥማቸው ወቅት ለቤተሰብና ለጓደኛ በማወያየት ጫናውን መቀነስ እንደሚችሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ከዛ በፊት ግን ከራስ ጋር መግባባት ያስፈልጋል።

በአሁኑ ወቅት ያለው የአገራችን ሁኔታ ሴቶችን ለከፍተኛ ጭንቀት የሚያጋልጥ ነው። ሴቶች በኹሉም ደረጃ ኃላፊነት ድርሻ ላይ የሚቀመጡበት ሁኔታ ሰፊ ከመሆኑም ባሻገር የሚደርስባቸውን ውጥረት ይበልጥ ያሳድገዋል።
በጭንቀት ውስጥ ያሉ ሴቶችን ለመረዳት ማሕበረሰቡ የበኩሉን ድርሻ መወጣት ይኖርበታል። ከነዚህም መካከል የጭንቀቱን መንስኤ ማወቅ ይቀድማል። ይህም ለተጨነቁ ሴቶች የመፍትሄ ሐሳብ ለማቅረብ በር ይከፍታል።
አንዳንድ ጊዜ ሴቶች የሚያስጨንቃቸው ምክንያት ስለሚለያይ ያካፈሉንን ጭንቀት ምክንያት ከኛ አስተሳሰብ ጋር ማነጻጸርና ማቅለል ተገቢ አይደለም።

ለጭንቀት ተጋላጭ የሆኑ ሴቶችን በቅርብ በማገዝ በተቻለ አቅም መርዳት አስፈላጊ ነው። ሁኔታው ከባድ የሚባል ደረጃ ላይ ከደረሰ ወደ ሕክምና እና ዕምነት ተቋማት መውሰድ እና እንዲረጋጉ ማድረግ ተመራጭ ነው።
በሕይወት መንገድ ላይ ከሚደርሱ ችግሮች አንዳንዶቹን ለመፍታት ከሰው ልጅ አቅም በላይ የሚሆንበት ሁኔታ ስለሚያጋጥም አንዳንድ ጊዜ ሊቀየሩ የማይችሉ ችግሮችን ተቀብሎ መኖር አስፈላጊ ነው። እርስዎስ ምን ይላሉ? በሕይወትዎ የሚያጋጥሙ ችግሮችን መፍታት ይችላሉ?


ቅጽ 3 ቁጥር 143 ሐምሌ 24 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here