በኅዳሴው ግድብ ዙሪያ ቀጣይ ውይይት በካይሮ ሊካሔድ ነው

Views: 494

በታላቁ ኅዳሴ ግድብ ዙሪያ የላይኛው ተፋሰስ አገራት ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በቀጣይ ሳምንት ኅዳር 22 እና 23 በግብጽ ዋና ከተማ ካይሮ ለውይይት እንደሚቀመጡ ተገለፀ። ምንጮች ለአዲስ ማለዳ እንዳስታወቁት በግብጽ ካይሮ የሚካሔደው ይህ ውይይት ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተደረገው ቀጣይ ክፍል እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

እስከ መጪው ግንቦት 2012 ድረስ አራት ውይይቶችን ለማድረግ ዕቅድ የተያዘ ሲሆን ከዚህ ቀደም አንድ ውይይት በአዲስ አበባ መደረጉ የሚታወስ ነው። በዚህ ውይይት ላይም የዓለም ባንክ እና የአሜሪካ ታዛቢዎች እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል። ከሳምንታት በፊት የሦስቱ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች በአሜሪካ ዋሽንግተን በመገኘት ጥንካራ ውይይቶችን በማድረግ የተለያዩ ሲሆን እስከ መጪው ግንቦት ድረስ አራት ውይይቶች እንዲደረጉ ተወስኖ ኅዳር 4 እስከ 6/2012 በአዲስ አበባ ውይይት ተደርጓል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com