የ10000 ሜትር ወንዶች ውጤትን በማስመልከት የኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳት ክብርት ኮ/ር ደራርቱ ቱሉ መልዕክክት አስተላልፋለች።
“በጃፓኗ-የቶኪዮ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው 32ኛ የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ የአትሌቲክሰ ውድድር በተጀመረበት እለት በ10000 ሜትር ወንዶች የፍፃሜ ውድድር በአትሌት ሰለሞን ባረጋ ለሃገራችንን ባመጣው የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳልያ እጅግ ደስ ብሎናል፡፡”
“ለመላው የሃገራችንን ህዝቦች በራሴና በኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ፌደረሽን ስራ አስፈፃሚና ማኔጅመንት ኮሚቴ፣ አሰልጣኞች፣ ኦፊሻሎችና ሰራተኞች ስም በድጋሚ እንኳን ደስ አለን እያልኩኝ ላለፉት ስምንት የዝግጅት ወራት ከጎናችን ለነበራችሁ በሙሉ ምስጋናዬ የላቀ ነው ድሉ ይቀጥላል፡፡
የሃገራችንን ክብር በአትሌቲክሰ ጀግኖቻችን ገና ከፍ ይላል!!!”




