የበረራ አስተናጋጆቹ ሕገ ወጥ መድኃኒቶችን ይዘው ሊገቡ ሲሉ ተያዙ

0
413

ለስንፈተ ወሲብ፣ ለጸጉር እድገት እና ለካንሰር ሕመም ይውላሉ የተባሉ ሕገ ወጥ መድኃኒቶችን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አስተናጋጆች በቦሌ ዓለም ዐቀፍ አየር ማረፊያ በኩል ይዘው ሊገቡ ሲሉ መያዛቸው ተሰማ።

አዲስ ማለዳ ከምንጮቿ እንደሰማችው ሰራተኞቹ የአየር መንገዱ ቢሆኑም፤ ሕገ ወጥ ድርጊቱን በመፈጸም ተጠርጥረው የተያዙት ግለሰቦች ብዛት ግን ምን ያክል እንደሆነ በውል አልታወቀም።

የኢትዮጵያ የምግብ፣ መድኃኒት፣ ጤና ክብካቤ ቁጥጥርና አስተዳደር ባለሥልጣን እንደገለጽው፤ መድኃኒቶቹ ቪማክስ፣ ሲስቶን እና ሚኖክሲድል የሚባሉ ሲሆን በኢትዮጵያ ያልተመዘገቡና ጥራታቸው ያልተረጋገጠ ነው።

መድኃኒቶቹ ከሕገ ወጥ ወኪሎች በኩል የገቡ በመሆኑ የኅብረተሰቡ ጤና ላይ ጉዳት ሊያደርሱ እንደሚችሉ ነው ባለሥልጣኑ ያሳሰበው።
ተጠቃሚዎች በዚህ ረገድ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የመከረው ባለሥልጣኑ፣ ሕገ ወጥ ድርጊቱ በሕጋዊ መንገድ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን እየጎዳ ስለመሆኑም አስገንዝቧል።

ቅጽ 1 ቁጥር 11 ጥር 18 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here