የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርስቲ በተማሪዎች ጥያቄ ለ15 ቀናት እንዲዘጋ ተወሰነ

Views: 223

በምስራቅ ሐረርጌ የሚገኘው የኦዳ ቡልቱም ዪኒቨርስቲ በተማሪዎች ጥያቄ መሰረት ለ15 ቀናት ዝግ ሆኖ እንዲቆይ መወሰኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ደቻሳ ጉርሙ ለአዲስ ማለዳ ገልፀዋል።

ደቻሳ ጨምረው እንደገጹት ከግቢው ተማሪዎች ጋር  ውይይት በተደረገበት ወቅት ከተማሪዎች በተነሳው ጥያቄ ከሰሞኑ አጋጥሞ በነበረው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ ‹‹ለተወሰኑ ቀናት መረጋጋት ያስፈልገናል››የሚል ሃሳብ በመበራከቱ ምክንያት ለአስራ አምስት ቀናት ምንም አይነት የመማር ማስተማር ሂደት እንደማይኖር ለማወቅ ተችሏል።

በዩኒቨርስቲው ውስጥ ለመቆየት የሚፈልጉ ተማሪዎች ካሉም ዩኒቨርስቲው ምግብና መኝታ እንደማይጓደልባቸው አስታውቋል።

በአከባቢው ለግጭት መነሻ የሆነውን ለማጣራት እና አስተዳደራዊ ችግሮችን ለመፈታት የተማሪዎቹን ሃሳብ በመቀበል ውሳኔ እንደተሰጠበት ተናግረዋል።

ግጭት ተከስቶባቸው በነበሩ የተለያዩ የአገሪቱ ክልል ዩኒቨርስቲዎች ያለው የሰላም ሁኔታ እየተረጋጋ በመምጣቱ  የመማር የማስተማር ሂደት መጀመሩ ይታወቃል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com