የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2011 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት 9 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታውቋል።
ይህም ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ብልጫ ማሳየቱን ባንኩ ገልጿል። በተጨማሪም ከወጪ ንግድና ሐዋላ 3 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላርን ባለፉት ስድስት ወራት ወስጥ መሰብሰቡን አስታወቋል።
በግማሽ ዓመቱ የባንኩ አጠቃላይ ተጨማሪ ተቀማጭ ገንዘብም ወደ 29 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ማደጉ ታውቋል።
40 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ብድር መስጠቱን የገለጸው ባንኩ፥ 3 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ክፍያ ለደንበኞቹ መፈጸሙንም ገልጿል።
ቅጽ 1 ቁጥር 11 ጥር 18 ቀን 2011