የመሰረተ ልማት አውታሮች ችግር የኃይል ብክነት እያደረሰ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ

0
473

የመሰረተ ልማቱ ማርጀት እና ከፍተኛ ኃይል መሸከም ብክነትን እንደሚፈጥር ያነሱት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር መላኩ ታዬ ኔትወርኩ ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች እና ውድመቶች እንዲሁም ስርቆቶች ለብክነቱ ተጠቃሽ ምክንያቶች እንደሆኑ ገልጸዋል።
ኃይልን በአግባቡ መጠቀም አለመቻል አሁንም የሚስተዋል መሰረታዊ ችግር መሆኑን ያነሱት መላኩ ደረጃቸውን ያልጠበቁ እቃዎች ከፍተኛ ለሆነ የኃይል ብክነት ምክንያት እንደሆኑ አንስተዋል።
በቤት ውስጥ የኃይል አጠቃቀም ሰዓትን አለመለየት ሌላው የኃይል ብክነትን እያመጣ ያለ ችግር በመሆኑ ጉዳቱ በተቋሙ ብቻ የሚያበቃ ሳይሆን ተጠቃሚውንም ለከፍተኛ ወጪ የሚዳርግ እንደሆነ ተናግረዋል።
ተቋሙ ኔትወርክ የማሻሻል እና የመልሶ ግንባታ ስራ በስፋት እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቅሰው በአዲስ አበባ እና ዙሪያው ባሉ አካባቢዎች ሶስተኛው ምዕራፍ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ ማሻሻያው ሊደረግላቸው ከታቀደባቸው የክልል ከተሞች ከአዲግራት ውጪ በሁሉም አካባቢዎች በስፋት ግንባታው እየተከናወነ እንዳለ ጠቁመዋል። አዲስ የሚገነቡት መሰረተ ልማቶች የኃይል ብክነቱን ሊቀንሱት እንደሚችሉ አስታውቀዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 145 ነሐሴ 8 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here