በአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ በሀምሌ ወር ብቻ ከ5.8 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

0
560

የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ከሀምሌ 01 እስከ ሀምሌ 30/2013 ዓም በሶስቱም ደረጃ ግብር ከፋዮች 5 ቢሊዮን 820 ሚሊየን 260 ሺሕ ብር መስብሰቡን አስታውቋል። ቢሮው በተጠቀሰው ጊዜ 5 ቢሊዮን 390 ሚሊዮን 930 ሺሕ ብር ለመሰብሰብ አቅዶ የነበረ ሲሆን፤ 5ቢሊዮን 820 ሚሊየን 260 ሺሕ ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 108 በመቶ መሰብሰቡን ገልፀዋል።
ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 1 ቢሊዮን 126 ሚሊዮን 950 ሺሕ ብር ወይም 24 በመቶ ብልጫ እንዳለው የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ሙሉጌታ ተፈራ ተናግረዋል።
ከሀምሌ 1/2013 እስከ ጥቅምት 30/2014 ዓም ድረስ ዋነኛ የግብር ማሳወቂያና መክፈያ ወቅቶች እንደሆኑ የተናገሩት ሙሉጌታ በተለይም ወርሃ ሐምሌ ደግሞ የደረጃ “ሀ እና ለ” ግብር ከፋዮች እንደተጠበቀ ሆኖ የደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች ግብሮቻቸውን የሚከፍሉበት ብቸኛ ወር መሆኑም ጠቁመዋል።
እንደ ኃላፊው ገለጻ በተጠናቀቀው የ2013 በጀት ዓመት በከተማዋ 42 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉ ያነሱ ሲሆን አፈፃፀሙም ባለፉት 8 ዓመታት ከተሰበሰው ገቢ የላቀ መሆኑን ከከተማው ፕሬስ ሴክሬታሪያት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።


ቅጽ 3 ቁጥር 145 ነሐሴ 8 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here