በአጣዬ የወደሙ ቤቶች መልሶ የመገንባት ሥራ መጀመሩ ተገለጸ

0
582

በአጣዬ ከተማ አሥተዳደር የወደሙ ቤቶችን መልሶ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ይፋት ልማት ማኅበር የአስር ቤቶችን ግንባታ ማስጀመሩ ተገለጸ። የልማት ማኅበሩ በአጣዬ፣ ኤፍራታና ግድም ወረዳ ኹለት መቶ ቤቶችን ለመገንባት አቅዶ ወደ ተግባር መግባቱ ነው የተገለጸው።
የልማት ማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ ክፍሉ ቢፈሩ፣ ማኅበሩ አንድ መቶ ሚሊዮን ብር መድቦ ቤቶችን የመገንባት ሥራ መጀመሩን ተናግረዋል ። ዛሬ ግንባታቸው የተጀመሩ አስር ቤቶችም በዘጠኝ ነጥብ ሰባት ሚሊየን ብር እንደሚገነቡ ተገልጾ ግንባታቸው በአምስት ወራት እንደሚጠናቀቅ ዕቅድ ተይዟል ነው ያሉት።
የሰሜን ሸዋ ዞን ከተማ ልማትና ቤቶች ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ በድሉ ውብሸት በበኩላቸው፣ የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ከ1 ሺህ 400 በላይ በቀጣናው የወደሙ መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት እየተንቀሳቀሰ ነው ብለዋል።
በአካባቢው የደረሰውን ውድመት መልሶ ለማቋቋም ኹሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ ያቀረቡት የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አገኘሁ መክቴ ሲሆኑ፣ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም እየተሠራ መሆኑንም ተናግረዋል። በቀጣይም ሆቴሎችና ሌሎች የአገልግሎት ተቋማትን ለመገንባት መታቀዱ ተጠቁሟል።


ቅጽ 3 ቁጥር 150 መስከረም 8 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here