የአዋሽ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጸሐይ ሽፈራው ከ50 ምርጥ የአፍሪካ ባንኮች ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች አንዱ ሆነው ተመረጡ። በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የአመራር ኩባንያ የሆነው “Reputation Poll International” በዚህ ዓመት ሰዎችን በማገናኘት ፣ ንግዶችን በማገናኘት እና በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በኢኮኖሚው ላይ ተጽዕኖ ለሚያሳድረውና በሕዝብ ውስጥ ትልቅ ሚና ለሚጫወተው የባንክ ዘርፍ ዕውቅና ሰጥቷል።
“Reputation Poll International” ዓመታዊ የደረጃ አሰጣጡን ተግባራዊ ለማድረግ በአፍሪካ የባንክ ዘርፍ በተለያዩ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ላይ ሰፊ ምርምር አድርጎ የዓመቱ ምርጥ የባንክ መሪዎች ያላቸውን 50 የባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚዎችን ይፋ አድርጓል፡፡
ተቋሙ እነዚህን መሪዎች ለመምረጥ በባንክ ዘርፉ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የነደፉትን ስትራቴጂዎችን እና ተግባራዊ ለማድረግ የተጫወቱትን ወሳኝ ሚና፣ ልህቀት ፣ ታማኝነት ፣ አስተማማኝነት ያለው የባንክ አገልግሎት፣ ያላቸውን ባለሙያ ፣ ቴክኖሎጂ እና የብድር አሰጣጥና አስተዳደርን በመመዘኛነት ተጠቅሟል፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የአመራር ኩባንያ የሆነው “Reputation Poll International. ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ እያሽቆለቆለ ያለው የባንኮች ትርፋማነት የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የሚያስችሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር በዘርፉ ታይቶ የማይታወቅ ፈጠራ እንዲነቃቃ ምክንያት ሆኗል ተብሏል።
ቅጽ 3 ቁጥር 150 መስከረም 8 2014


