10ቱ ከፍተኛ የውጭ ብድር ያለባቸው የምሥራቅ አፍሪካ አገራት

Views: 386

በአፍሪካ ይልቁንም በምሥራቅ አፍሪካ የሚገኙ አገራት የገንዘብ እጥረታቸውን የሚሞሉት በብድር ነው። ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው መሠረተ ልማቶችንም በብድር ሸፍነዋል። ታድያ ከአበዳሪዎች መካከል ቻይና ቀዳሚውን ስፍራ ስትይዝ፣ የምሥራቅ አፍሪካ አገራት የቻይና ባለ ዕዳ ሆነዋል። ይህ ብድር ውድ ቢሆንም አፍሪካ በተለይም ምሥራቁ ክፍል ያሉ አገራት ሳይታወቃቸው ከራሳቸው ኪስ የመውሰድ ያህል ተደራሽና ቀላል ስለሆነ ክብደቱን እምብዛም ትኩረት የሰጡት አይመስልም።

በዚህ መሠረት ከፍተኛ ባለዕዳ በጥቅሉም በምሥራቅ አፍሪካ ብዙ ዕዳ ያለባት አገር ሱዳን ሆና ተመዝግባለች። የአፍሪካን ልማት ባንክ ባስነበበው ዘገባ ላይ፣ የሱዳን ዕዳ 55.4 ቢሊዮን ዶላር ነው። ከሱዳን ቀጥሎ ኬንያ በ42.7 ቢሊዮን ዶላር በኹለተኛ ደረጃ ባለ ዕዳ ሆና ተቀምጣለች። ኤርትራ እና ቡሩንዲ በአስርቱ ዝርዝር የመጨረሻዎቹ ላይ የተቀመጡ ሲሆን፣ 1.3 እና 0.5 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ ይዘዋል።

በዚሁ ዘገባ መሠረት ታድያ፤ ኢትዮጵያ ከሱዳን በእጥፍ በሚያንስ የገንዘብ መጠን ሦስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ኢትዮጵያ ካላት ዓመታዊ ጥቅል ምርት አንጻርም ዕዳዋ 30.5 በመቶ ነጥብ አስመዝግቧል።

ቅጽ 2 ቁጥር 60 ታኅሣሥ 18 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com