4 የተመድ ሰራተኞች በ72 ሰአታት ውስጥ ከአገር እንዲወጡ የኢትዮጵያ መንግስት ትእዛዝ አስተላለፈ

0
819

የኢትዮጵያ መንግሥት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስር በተለያዩ ኤጀንሲዎች ውስጥ የሚሰሩ 4 የውጭ አገር ዜጎች በ72 ሰዓት ውስጥ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ ትእዛዝ ማስተላለፉን የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የኢትዮጵያን ድንበር ለቀው እንዲወጡ የታዘዙት የመንግሥታቱ ድርጅት ባልደረቦች በአገር ውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ህገ ወጥ ሥራ ሲሠሩ የተገኙ መሆናቸውም ነው የተገለፀው።

የኢትዮጵያን ድንበር ለቀው እንዲወጡ የታዘዙት የውጭ አገር ዜጎች የዩኒሴፍ የኢትዮጵያ ተወካይ ሚስ አዴል ኮርድ፣ የተራድኦ ምክትል አስተባባሪ ግራንት ሊያቲ፣ የተራድኦ ምክትል አስተባባሪ ተወካይ ሚስ ጋዳ ኤልታሂር ሙዳዊ እና የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ምክትል አስተባባሪ ሰኢድ መሀመድ ሀርሲ መሆናቸውም ተገልጿል።
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here