በቅርቡ ከብድር አቅርቦት ጋር በተያያዘ የጣለውን ገደብ ታሳቢ ያደረገ ማሻሻያ በማድረግ፣ ባንኮች አምስት የብድር ዓይነቶችን መፍቀድ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።
ብሔራዊ ባንክ ዓርብ መስከረም 21/ 2014 ለባንኮች ባስተላለፈው መልዕክት እንዳስታወቀው፣ ባንኮች የሰጡትን ብድር ለማስመለስ ሐራጅ ያወጧቸውን ንብረቶች ለመግዛት ለሚጠይቁ ገዥዎች ብድር መስጠት ይችላሉ ብሏል፡፡
ብሔራዊ ባንክ ብድር ይፈቀዱ ያላቸው በሁለተኛና በሦስተኛ ወገኖች መካከል የሚደረግ ግብይትና ለባንክ ሠራተኞች የሚሰጥ አስቸኳይ ብድር መሆኑንም አስታውቋል፡፡
ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልተው የመኖርያ ቤት ለመግዛት ወይም ለመገንባት ከታመነባቸውና ከፀደቁ ድርጅቶችና ከተቋም ሠራተኞች ለሚቀርቡ የብድር ጥያቄዎች፣ አዎንታዊ ምላሽ መስጠት የሚችሉ መሆኑን ብሔራዊ ባንክ ለባንኮች የላከው ማሻሻያ ያመለክታል፡፡
ሌላው ባንኮች ብድር መፍቀድ ይችላሉ የተባለው በጎንደር አካባቢ ለሚገኙ የሰሊጥ አምራቾች ነው፡፡ ወቅቱን የጠበቀ ሰሊጥ ለማምረት እንዲችሉ ታምኖበት በጎንደር አካባቢ ለሚገኙ አምራቾች እንዲቀርብ የፀደቀ የብድር ዓይነት እንዲለቀቅ መወሰኑንም ማስታወቁን ሪፖርተር ዘግቧል።
__________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n




