ምርት ገበያ በ5 ወራት የ12 ቢሊዮን ብር ምርቶችን ለገበያ አቀረበ

Views: 779

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በታኅሳስ ወር 5 ነጥብ 12 ቢሊየን ብር ዋጋ ያላቸው 101 ሺሕ 948 ቶን ምርቶችን ማገበያየቱን ገለፀ። ምርቶቹም ሰሊጥ፣ ቡና፣ ነጭ እና ቀይ ቦሎቄ ናቸው።

በታኅሳስ ወር ለግብይት ከቀረበው 52 ሺሕ 598 ቶን ሰሊጥ በ2 ነጥብ 24 ቢሊየን ብር ሲያገበያይ፣ የሁመራ ጎንደር ሰሊጥ 90 በመቶ የግብይት መጠንና የዋጋ ከፍተኛ ድርሻ ይዟል። ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም የግብይት መጠኑ በ34 በመቶ እንዲሁም የግብይት ዋጋው በ26 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን፥ አማካይ ዋጋው ግን በአምስት በመቶ ቀንሷል።

የቡና ግብይት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀር የግብይት መጠኑ በ10 በመቶ፣ የግብይት ዋጋው ደግሞ በ31 በመቶ እንዲሁም አማካይ ዋጋው በ24 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

በሌላ በኩል 1 ሺሕ 876 ቶን አኩሪ አተር ለግብይት ቀርቦ በ22 ሚሊዮን ብር ተገበያይቷል። ይህም ካለፈው ወር ጋር ሲነፃፀር በመጠን 73 በመቶ በዋጋ 36 በመቶ ጨምሯል። በአጠቃላይም በግብይቱ የጥራጥሬና የቅባት እህል ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር መሻሻል እንዳሳየ ምርት ገበያው አስታውቋል።

በተጨማሪም ምርት ገበያው የበቆሎ ምርትን ከ11 ዓመት በኋላ ዳግም ለማገበያየት የግብይት ኮንትራቱን ለማሻሻል እና የመጋዘን ብድር አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 62 ጥር 2 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com