አማራ ባንክ አክሲዮን ማኅበር የሼር ሽያጭ ጊዜውን እስከ የካቲት 30 አራዘመ

Views: 1079

በምሥረታ ላይ የሚገኘው አማራ ባንክ አክሲዮን ማኅበር የአክሲዮን ሽያጭ ጊዜውን እስከ የካቲት 30/2012 ማራዘሙን አስታወቀ።

በምስረታ ላይ የሚገኘው ባንኩ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ባለሃብቶች አክሲዮን የመግዛት ፍላጎት ማሳየታቸውን ተከትሎ፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን የአክሲዮን ባለቤት ለማድረግ በማሰብ የሽያጭ ጊዜውን ማራዘሙን አስታውቋል።

የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን አክስዮን እንዲገዙ እድል ለመሥጠት እንዲቻል ከብሔራዊ ባንክ በመዘጋጀት ላይ ያለው ዝርዝር መመሪያ እስኪደርስ በሚሉ ምክንያቶች የመሥራችነት አክሲዮን ሽያጭ ሂደቱ እስከ ታኅሳስ 30/ 2012 ድረስ ተራዝሞ ነበር። ሆኖም አሁንም ተመሳሳይ ዕድልን ለመስጠት ለመጨረሻ ጊዜ እስከ የካቲት 30 እንዲራዘም ተደርጓል።

አማራ ባንክ አክሲዮን ማኅበር ካለፈው ዓመት ነሐሴ 11/ 2011 ጀምሮ የአክሲዮን ሽያጭ ሲያከናውን የቆየ ሲሆን፣ ከ70 ሺሕ በላይ የሚሆኑ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ተሳትፈው የተፈረመ 4 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር እንዲሁም የተከፈለ 3 ቢሊዮን ብር መድረሱን ባንኩ ገልጿል።

ቅጽ 2 ቁጥር 62 ጥር 2 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com