10ቱ በርካታ ቅርንጫፍ ያላቸው በኢትዮጵያ የሚገኙ የግል ባንኮች

Views: 183

በኢትዮጵያ ባንኮች፣ ኢንሹራንስ ኩባንያዎች እንዲሁም አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት የገንዘብ እንቅስቃሴውን በቀዳሚነት ይዘውሩታል። ይልቁንም ብዛት ያላቸው ባንኮች በአገር ደረጃ በተለያዩ ከተሞችና ክልሎች በስፋት ቅርንጫፎቻቸውን የከፈቱ ሲሆን፣ በ2018/19 በጀት ዓመት 807 አዳዲስ ቅርንጫፎች መከፈታቸውን ዓመታዊው የብሔራዊ ባንክ ዘገባ ያስረዳል። ይህም ቀድሞ ከነበረው 4 ሺሕ 757 ቅርንጫፍ ወደ 5 ሺሕ 564 እንዲያድግ አድርጓል። በዘገባው መሠረት ታድያ ከግል ባንኮች ውስጥ በብዛት ቅርንጫፍ ያለው አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ነው። በመላው አገሪቱ 423 ቅርንጫፎች ያሉት ባንኩ፣ በክልል ካሉት (245) ቅርንጫፎች አንጻር ከዳሽን ባንክ (265) ቀጥሎ በኹለተኛነት ይከተላል።

በአንጻሩ በአዲስ አበባ 178 ቅርንጫፎችን በመክፈት በቀዳሚነት ተቀምጧል፤ አዋሽ ባንክ። ከአስርቱ ዝርዝር ጥቂት የቅርንጫፍ ብዛት ያሉት ተብሎ የተመዘገበው በ209 ቅርንጫፎች ቡና ባንክ ይሁን እንጂ፣ ዘመን ባንክ (44) እንዲሁም እናት ባንክ (45) በቅርንጫፍ ብዛት በኢትዮጵያ ካሉት ባንኮች አነስተኛ ቅርንጫፍ ያላቸው ሆነው ተመዝግበዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ይፋ ባደረገው በዚህ ዓመታዊ ዘገባ ላይ እንዳካተተው ታድያ፤ በድምሩ 18 ባንኮች በኢትዮጵያ የሚገኙ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 16ቱ የግል ናቸው። በተጓዳኝ 17 የኢንሹራንስ ኩባንያዎች፣ 38 ደግሞ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት አሉ ተብሎ ተመዝግቧል። የሕዝብ ወይም የመንግሥት ከሚባሉ ባንኮች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚጠቀሱ ሲሆን፣ በበጀት ዓመቱ ንግድ ባንክ 1 ሺሕ 578 ልማት ባንክ ደግሞ 107 ቅርንጫፎችን ከፍተው ለደንበኞቻቸው ተደራሽ ለመሆን ሠርተዋልሰ።

ቅጽ 2 ቁጥር 64 ጥር 16 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com