አንድ የፖሊስ አባል የቀድሞ ፍቅረኛውን እና የራሱን ሕይወት አጠፋ

Views: 911
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ቶታል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ቅዳሜ ጥር 23 /2012 አመሻሽ 11 ሰዓት አንድ አካባቢ አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል የቀድሞ ፍቅረኛውን እና የራሱን ሕይወት በጠመንጃ እንዳጠፋ የክፍለ ከተማው ፖሊሰ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ኃላፊ ኢንስፔክተር ተዘራ ክፍያለው ለአዲሰ ማለዳ ገለጹ።
 
ግለሰቡ ከእኔ ሌላ ፍቅረኛ ይዛለች በሚል ጥርጣሬ እና ከዚህ ቀደም በነበራቸው አለመግባባት የተነሳ፣ የቀድሞ ፍቅረኛው ቤተሰቦቿ በከፈቱላት የመዋቢያ መደብር ውስጥ በመግባት በተኮሰው ሦስት ጥይት ሕይወቷ ሊያልፍ እንደቻለም ምክትል ኢንስፔክተሩ አስታውቀዋል። እንዲሁም የራሱን ሕይወት ወደ አንገቱ በተኮሰው ኹለት ጥይት ያለፈ ሲሆን የኹለቱም ሕይወት ሆስፒታል ሳይደርሱ እዚያው ማለፉንና በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በኩል አስከሬናቸው ወደ ምኒልክ ሆስፒታል ተልኮ ምርመራ መከናወኑንም አክለዋል።
 
የሟች ምሕረት አድማሱ የቀብር ስነ ስርዓትም፣ ባሳለፍነው እሁድ ጥር 24/2012 ከሰዓት በኋላ ቃሊቲ በሚገኘው ሳለ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን እንደተፈጸመ አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የሟች አብሮ አደግ ገልፀዋል።
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com