የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከጀመረ አንስቶ ከኹለት ሴቶች በአንዷ ላይ ጥቃት እንደተፈፀመ ተገለጸ

0
574

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሴቶች ጉዳይ የሚከታተለው ‹‹UN Women›› ያወጣው አዲስ ሪፖርት ወረርሽኙ በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን አባብሷል ሲል አትቷል፡፡
ድርጅቱ ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት በመቃወም በሚካሄደው የ16 ቀን ዘመቻ ማስጀመሪያ ዋዜማ ላይ ይፋ ባደረገው አዲስ ሪፖርት እንዳመለከተው ከሆነ፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከጀመረ አንስቶ ከኹለት ሴቶች በአንዷ ላይ ጥቃት ደርሶባታል፤ አሊያም ከሚያውቋቸው ኹለት ሴቶች አንዷ ላይ ጥቃት አጋጥሟታል።
እንዲሁም፣ በቤት ውስጥ በአዋቂዎች መካከል የሚፈጠሩ ግጭቶች፣ ማስፈራሪያ እና አካላዊ ጥቃቶች በመጨመራቸው ሴቶች በቤት ውስጥ ብዙም ደኅንነት እንደማይሰማቸው ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡ እንደ ሪፖርቱ ገለጻ ከአስር ሴቶች ሰባቱ ወረርሽኙ ከተከሰተ አንስቶ የቤት ውስጥ ጥቃት እንደጨመረም ያምናሉ።
ከአምስት ሴቶች ሦስቱ ደግሞ ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች የሚፈፀም ወሲባዊ ትንኮሳ ተባብሷል ብለው ያስባሉ። ይህም ወረርሽኙ ከጀመረ አንስቶ ሥራ እንዳይሠሩ፣ መሠረታዊ እና መዝናኛ አገልግሎቶች እንዳያገኙ ማድረጉን ነው ሪፖርቱ የገለጸው፡፡
ወረርሽኙ ከተከሰተ አስንስቶ ከ13 አገራት በተሰበሰበ መረጃ ላይ ተመስርቶ የወጣው ይህ ሪፖርት፣ ከወረርሽኙ በኋላ ጥቃት እንደደረሰባቸው የተናገሩ አሊያም የደረሰባቸው ሴቶች ዝቅተኛ እና ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን አገራት ለይቷል።


ቅጽ 4 ቁጥር 160 ሕዳር 18 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here