ኹሉም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለአንድ ሳምንት ዝግ እንዲሆኑ ውሳኔ ተላለፈ

0
475

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች የትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር ባደረጉት የጋራ ውይይት ይህ ውሳኔ የተላለፈ መሆኑ ታውቋል።
ይህን ተከትሎም በመላ አገሪቱ የሚገኙ ኹሉም ትምህርት ቤቶቹ ከኅዳር 27 እስከ ታህሳስ 3 ቀን 2014 እንደሚዘጉና ተማሪዎች፣ መምህራን እና ሠራተኞች ለዚህ አገራዊ ትግል እንደየ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ መወሰኑ ታውቋል።
ትምህርት ቤቶቹ ዝግ በሚሆኑበት ወቅትም ያልተሰበሰቡ የዘማች ሰብሎችን መሰብሰብና ቤተሰብን የመርዳት ዘመቻዎች በሥፋት እደሚያካሄዱም የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣው መረጃ ያመለክታል።
በዚህ ሒደት ትምህርት የቆመባቸው ቀናት በሙሉ ትምህር ቤቶች በሚያወጡት የማካካሻ መርሃ-ግብር መሠረት እንዲካካሱ ይደረጋሉም ነው የተባለው።
አገር ከሌለች መኖር ስለማይቻል ኹሉም አገሩን የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት፣ ስለዚህም የትምህርት ሴክተሩ ያለበትን አገራዊ ኃላፊነት ይወጣል በሚል ውሳኔ ላይ መደረሱ ተሰምቷል።
ከዚህ ባሻገር በትምህርት ዘርፉ ውስጥ ያሉ አካላት ገንዘብ በማዋጣት፣ ደም በመለገስ፣ ስንቅ በማዘጋጀት እንዲሳተፉም ውሳኔ ተላልፏል። ተማሪዎችም በዚህ ወቅት አገራዊ ግዴታቸውን በመወጣት አገሪቱን ለመገንባት በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ እንዲሳተፉም ጥሪ ቀርቧል።


ቅጽ 4 ቁጥር 161 ሕዳር 25 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here