የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2021 የቢዝነስ ተጓዦች የአፍሪካ ምርጥ አሸናፊ ሆነ ተባለ

0
587

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2021 የቢዝነስ ተጓዦች ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ ሽልማት አሸናፊ ሆኗል ተባለ።
በአፍሪካ ግዙፍ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆነው “ቢዝነስ ትራቭለርስ” መጽሔት የሚያዘጋጀውን ሽልማት ነው በምርጥነት ያሸነፈው ተብሏል።
ከዚህም በተጨማሪ የ2014 ዓመት ሽልማት የ24 ወራቶች የደንበኞች ምልከታ ያሸፈነ መሆኑ ተዘግቧል።
በሌላ በኩል፣ በ2014 ዓመት በንግድ ተጓዦች የተሰጡ ድምጾች የአየር መንገዶችን የተግባቦትና የኮሮና ወረርሽኝ የጥንቃቄ ዕርምጃዎች ውጤታማነት ታሳቢ ያደረጉ እንደሆኑም ተብራርቷል ነው የተባለው።
በመሆኑም በተሳፋሪዎች አያያዝ፣ በሚጣልበት ዕምነት እና የቲኬት ለውጦችን በማድረግ ረገድ የሚኖረው ተባባሪነት፣ የወረርሽኙን ጊዜ ታሳቢ ያደረጉ ጥያቄዎች በሽልማት መስፈርትነት መካተታቸውም መመላከቱ ተነግሯል።
ይህ የላቀ ሽልማት የአየር መንገዱ የደንበኞች ዕርካታ ነጸብራቅ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተወልደ ገብረማርያም መናገራቸው ተዘግቧል።
በመሆኑም ሽልማቱ አየር መንገዱ በሁሉም ቦታ የላቀ የደንበኞች አገልግሎት ለማድረስ የሚያደርገውን ጥረት ስኬት የሚያሳይ በመሆኑ የሚያስደስት ነው ተብሏል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዚህም በተጨማሪ በ45 በመቶ ድርሻ በዛምቢያ መንግሥት ከሚተዳደረው “Industrial Development Corporation” ጋር በመተባበር የዛምቢያን ብሔራዊ አየር መንገድ አቋቁሞ ሥራ ማስጀመሩ ተዘግቧል።
በጋራ የመስራት ስምምነቱን አስመልክተውም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወልደ ገብረማርያም ማብራሪያ መስጠታቸው ተጠቁሟል።
ዘገባው እንዳመላከተው ከሆነ፣ “ስምምነቱ አየር መንገዳችን በ2025 ዕቅዱ ያስቀመጠው በአፍሪካ በርካታ የአቪዬሽን ቢዝነስ ማዕከል የመፍጠር ስትራቴጂ አካል ነው” ሲሉ ተወልደ ተናግረዋል ነው የተባለው።


ቅጽ 4 ቁጥር 161 ሕዳር 25 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here